ኢትዮጵያን በመጽሐፍ ቅዱስ እንሸፍናት


ሀገራችን ኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስን በመጀመሪያ ሙሉ ለሙሉ ያገኘችው በግዕዝ ቋንቋ እንደሆነ ከታሪክ መዛግብት ይነበባል።በተለይ በ 334 ዓም በአባ ሰላማ ጊዜ የተጀመረው የግዕዝ ትርጉም ሥራ በተሰዓቱ ቅዱሳን ተጠናቆ በግዕዝ መነበብ ጀመረ። ነገር ግን ግዕዝ እየተዳከመ ሄዶ ሕዝብን ሁሉ ለማገልገል የተመቻቸ ቋንቋ ስላልሆነ በአማርኛ ቋንቋ እየተተካ ሄደ። እግዚአብሔር ሀገራችንና ሕዝባችንን ለመባረክ በቃሉ እየተከታተለን ቃሉ ሊገባው በሚችል መንገድ ማቅረቡን አልተወም። ይህንን ለማከናወን የውጭ ሰዎች በ15ኛው ክፍለ ዘመን ላይ በአማርኛ ቋንቋ የዮሐንስን ወንጌል በመተርጎም ለማስነበብ ሞክረዋል።

ሆኖም እግዚአብሔር በልቡ ያለውን ሃሳብ ለመፈጸም በአንድ የጽድቅ ረሃብተኛ መነኩሴ አማካኝነት ያደረገው ታላቅ ሥራ ከሁሉ በላይ አስደናቂ ነው።መነኩሴው በ17ኛው ምዕተ ዓመት መገባደጃ ላይ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደው ተሳልመው ተመለሱ። እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ለመሳለም ሲጓዙ ግብጽ ላይ ታመው ቆዩ።በሕክምና የረዳቸው በግብጽ(ካይሮ) ውስጥ የነበረው የፈረንሳይ ቆንስላ አስሊን የተባለው ግለሰብ የአባ አብርሃምን የቋንቋ ችሎታ አይቶ መጽሐፍ ቅዱስን ከግዕዝ ወደ አማርኛ ቋንቋ እንዲተረጉሙ አደፋፈራቸው። እርሳቸውም ሃሳቡን ተቀብለው የመጀመሪያውን የአማርኛ ትርጉም በመሥራት(በመተርጎም) በእጃቸው እየጻፉ 9539 ገጽ አጠናቀቁ።ከዚያም ሕትመቱ እንግሊዝ ሀገር ተካሄደ።(ሙሉ ታሪኩን በሚቀጥለው ገጽ ይመልከቱ) እንግዲህ ከዚህ በኋላ መጽሐፍ ቅዱሱ ወደ ሀገራችን የገባው በውጭ ሚስዮናውያን እጅ በመሆኑ የእነርሱ እንደሆነ ተቆጠረ።

በባህሉና በቋንቋው ጠንካራ የሆነው ሕዝባችን በተለይ ከ12ኛው እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን በተለያየ መንገድ የሀገር ወረራ የተደረገበት በመሆኑ በውጭ ሰዎች የሚነገር ሃይማኖት ከሀገርና ከባህል ወረራ ጋር በማያያዝ በሀገሩ ሰው በተከበሩት በአባ አብርሃም የተተረጎመውን እጅግ ውድ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ እንኳን ለመቀበል ተቸግሮ ነበር። ሆኖም ነገሥታቱ ሁኔታውን አውቀውና ተረድተው በመቀበላቸው ሕዝቡን በጥበብ በተቻለ መጠን እንዲቀበል ለማድረግ ቋንቋው እየተሻሻለ ተነባቢነቱ እንዲጨምር ማድረግ ችለዋል። በተሻሻለው የአማርኛ ቋንቋ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ሊቃውንት ብርታት በብዛት ዛሬ ወደያዝነው መጽሐፍ ቅዱስ ደርሰናል። በተጨማሪ እግዚአብሔር ከአባ አብርሃም ቀጥሎ በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲተረጎም የተከበሩትን አናሲሞስ ነሲብንና ረዳታቸውን አስቴር ገኖን በማስነሳት ተጠቅሟል። ከዚያ ደግሞ የትግርኛው ተናጋሪ ሕብረተሰብ ቃሉን እንዲያነብ ደግሞ አለቃ ተወልደ መድኅን የተባሉትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅን በማስነሳት የትግርኛውን የትርጉም ሥራ አከናውነዋል።መጽሐፍ ቅዱስ መሰራጨት ከተጀመረ ጀምሮ በዓለም ላይ ብዙ ሰዎች የዘላለም ሕይወት ምን እንደሆነ ተረድተውማል አግኝተውማል። መጽሐፍ ቅዱስን ያነበቡ ሰዎች ሁሉ የሕይወት መለወጥ፣ የኑሮ መቀየር፣ የበሽታ ፈውስ ፣የመንፈስ መረጋጋትን፣ የልብ ስብራት መጠገንን፣ የብቸኝነትን መወገድንና የተመሰቃቀለ ኑሮን መስመር መያዝን ገጥሟቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ዛሬ በዓለም ላይ ከታተሙት መጻሕፍቶች ሁሉ በብዛት ተወዳዳሪ የሌለው ሲሆን በተጨማሪም በሕትመትም ደረጃ የመጀመሪያው ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ያነበቡ ነገሥታት በዓለም ያሉ የታወቁ መሪዎች ፈላስፎች አርትቲስቶች ጸሐፊዎች ሳይንቲስቶች ስለመጽሐፍ ቅዱስ የተለያየ አስደናቂ ነገር ጽፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ፍላጎት ያላቸው በአሁኑ ሰዓት ብዙ መጽሐፍ ቅዱስ ጠይቀውናል። 20ሺ መጽሐፍ ቅዱስ ለማሰራጨት ድጋፍ ጠይቀን እግዚአብሔር ረድቶን እየተሰራጨ ይገኛል። ይህንን ድጋፍ ያደረጋችሁልን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ሆኖም ራዕያችንን ለማሳካት በ 2017 40 ሺ መጽሐፍ ቅዱስ ለማሰራጨት ዕቅድ ይዘናል። ለዚህ ድጋፍ ለማድረግ የምትፈልጉ ሁሉ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ከ 100-120 የኢትዮጵያ ብር በመሆኑ ለአንድ መጽሐፍ ቅዱስ መግዣ የሚሆነውን ገንዘብ ባላችሁበት ሀገር ሂሳብ አስባችሁ በዚህ ድህረ ገጽ ላይ ባለ ድጋፍ መስጫ መንገድ በመጠቀም ከጎናችን እንድትቆሙ በአክብሮት በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። የተወደዳችሁ ወገኖች ከ5-7ዓመት ድረስ 350 ሺ መጽሐፍ ቅዱስ ለማሰራጨት ዕቅድ ስላለን የዚህን ሪፖርት በዚህ ድህረ ገጽ ላይ እንድትከታተሉ አደራ እንላለን።

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን አስተሳሰብ ወይም አእምሮ ያለማል፣ ልማት የሚጀምረው ከአእምሮአችን ነው፡፡ የሰው አእምሮ ከለማ ሀገርና ሕዝብ ይለማሉ፣ ቅዱስ ጳውሎስ‹‹ … በአእምሮአችሁ መንፈስ ታደሱ . . . ›› ኤፌሶን 4፥23 ስለሚል ስለሀገር ስለ ሕዝብ መታደስ ካሰብን አእምሮን የሚለውጥና ወደ ቀና የሀገርና የሕዝብ ፍቅርና ጥቅም በማንበብ ሰዎች እንዲለወጡ›› መጣር አለብን ይህንን ለመተግበር እንዲቻል የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ያሳተማቸውን መጽሐፍ ቅዱስ ለማሠራጨት በሚፈልግበት ቦታ ሁሉ ይህንን ጽሑፍ ማሠራጨቱ ጠቃሚ ነው ብለን እናምናለን፡፡

“ኢትዮጵያዊው አባ ሩሚ” (አባ አብርሃም)

“… ቅዱስ መጽሐፍ በ4ኛው ምእተ ዓመት በቅዱስ ፍሬምናጦስ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ቀጥሎም በ5ኛው ምእተ ዓመት በዘጠኙ ቅዱሳን በግሪክኛ ከተዘጋጀው ከሰባ ሊቃናት ትርጉም ወደ ግዕዝ ተተርጉሞአል፡፡ በዚህም የተቀደሰ ሥራ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ተሳትፈዋል፡፡

በተለይ በአባ ሰላማ ጊዜ ተክለ ሃይማኖትና ገብረ መስቀል የተባሉ ብሔራውያን ምሁራን በትርጒሙ ሥራ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳደረጉ በገድለ አብርሃና አጽብሓ ተመዝግቦአል፡፡ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ በተጠቀሱት አባቶች በዚህ ዓይነት ወደ ግዕዝ ከተተረጐመ በኋላ በወቅቱ የሕዝብና የቤተ ክርስቲያን መገልገያ በነበረው የግዕዝ ቋንቋ እየተነበበና እየተብራራ እስከ 17ኛው ምእተ ዓመት ቆይቶአል፡፡ በ17ኛው ምእተ ዓመት የአንድምታ ትርጓሜ ሊቃውንት በአንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍትን ወደ አማርኛ ለመተርጒም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ የእነዚህ ሊቃውንት ሥራ፣ በኋላ ለተሠራው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በር ከፋች ሆኖአል፡፡ እንደ እነ ጴጥሮስ ሄይሊንግ ያሉ አንዳንድ የውጭ ሀገር (ጀርመን) ሰዎችም ከ1628-1640 ዓ.ም ከቅዱሳት መጻሕፍት አንዳንድ ክፍሎችን እንዲሁም ተፈላጊ ወይም ምርጥ ጥቅሶችን ወደ አማርኛ ለመተርጐም ያደርጉት የነበረው ሙከራ ቀላል አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አማርኛ ለመተርጐም አልቀናቸውም፡፡ ቅዱስ መጽሐፍን በሙሉ ወደ አማርኛ ለመተርጐምና ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲያነበውና እንዲባረክበት ለማድረግ የቀናቸው የተከበሩ አባ አብርሃም ናቸው፡፡

አባ አብርሃም ማን ነበሩ?

ስዊድናዊው ዶ/ር ጉስታቭ አረን “ቀደምት ወንጌላውያን በኢትዮጵያ” በተባለው መጽሐፋቸው በገጽ 42-44 እንደገለጡት አባ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህን የሆኑ መነኵሴ ነበሩ፡፡ ምድረ ሙላዳቸውም ጐጃም እንደሆነ ዶ/ር ጉስታቭ አረን በጥናታዊ መጽሐፋቸውና አይዘንበርግም በአማርኛ መዝገበ ቃላታቸው ገልጠዋል፡፡ አባ አብርሃም በዐረብኛው አጠራር “አቡሩሂም፣ አቡሩህ፣ አቡሪም፣ አቢሩሚ” እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ ሁሉም አብርሃም ማለት ነው፡፡

አባ አብርሃም መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አማርኛ እንዴት ተረጐሙ?

አባ አብርሃም የ28 ዓመት ወጣት በነበሩ ጊዜ በግብፅ በኩል ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መንፈሳዊ ጉዞ አደረጉ፡፡ በኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናትን ከተሳለሙ በኋላ ወደ ሶርያ፣ አርማንያና ፋርስ ሄዱ፡፡ ከዚያም ወደ ሀገራቸው ወደ ኢትዮጵያ ከመመለሳቸው በፊት ወደ ሕንድ ሀገር ሄደው ነበር፡፡ ከሕንድ ወደ ሀገራችን ተመልሰው ለጥቂት ጊዜ ቆዩ፡፡ ያን ጊዜ የሃምሳ ዓመት ዕድሜ ሰው የነበሩት አባ አብርሃም ለሁለተኛ ጊዜ ገዳማተ ግብፅን ለመጐብኘት ወደ ግብፅ ተጓዙ፡፡ በካይሮ በነበሩበት ጊዜም በጽኑዕ ሕመም ታመው ነበር፡፡ ነገር ግን ከእርሳቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በነበረው በፈረንሳዊው አስሊን እርዳታ ከሞት ሊያመልጡ ችለዋል፡፡ አባ አብርሃም የዐረብ፣ የፋርስ፣ የኢጣልያ፣ የግሪክና የሌላም ሀገር ቋንቋዎችን ያውቁ እንደነበረና የኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ሊቅ እንደ ነበሩ ዶ/ር ጉስታቭ አብራርተው ጽፈዋል፡፡ በግብፅ የፈረንሳይ ኤምባሲ ምክትል ቆንስላ የነበረው አስሊን የአባ አብርሃምን ሊቅነት ከተረዳ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ አማርኛ በሙሉ እንዲተረጒሙ አማከራቸው፡፡ አባ አብርሃምም የአስሊንን ምክር በደስታ ተቀብለው የትርጒም ሥራቸውን ቀጥለዋል፡፡ ምክትል ቆንስላ አስሊንም ለአባ አብርሃም የቍሳቁስ ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጎአል፡፡

አባ አብርሃም የአስሊን ድጋፍ ሳይለያቸው የብሉይና የሐዲስ ኪዳናትን መጽሐፍ ቁጥር በቁጥር በታላቅ ጥንቃቄ የመተርጐም ሥራቸው ዐሥር ዓመታት ወስዶባቸዋል፡፡ አባ አብርሃም በግዕዝ ያልተብራሩ አስቸጋሪዎች ቃላትንና ሐረጎችን ባገኙ ጊዜ አስሊን በመሠረታዊው ቋንቋ በዕብራይስጥ የተጻፈውን ዘርዕ የሱርስቱንና የሰባ ሊቃናቱን ትርጒም እንዲሁም የቃላት መፍቻዎችንና ትርጓሜዎችን በመመልከት ይተባበራቸው ነበር፡፡ ከዚህም ሁሉ ጋር አባ አብርሃም በተለያዩ ቋንቋዎች የተጻፉትን ያነቡ ስለነበር የትርጒም ሥራቸው በዐጭር ጊዜ ተቃንቶላቸዋል፡፡ አባ አብርሃም ታላቁን ሥራቸውን እንደ ፈጸሙ በኢየሩሳሌም ዕረፍት ለማድረግ፣ በዚያ ለመሞትና ለመቀበር ተመኙ፡፡ ይህም ምኞታቸው የአካባቢውን ሃይማኖታዊ ሁኔታ ለመመርመር ወደ ቅርብ ምሥራቅ ተጒዞ የነበረው የስዊስ ቄስ ክርስቶፎር ቡርክሐርድት በመጋቢት 25 ቀን 1811 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ተረጋግጦአል፡፡ ቄስ ክርስቶፎር በመቀጠል አባ አብርሃም ኢየሩሳሌም አንደ ደረሱ በወረርሽኝ በሽታ መያዛቸውንና ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ገልጦ ጽፎአል፡፡ የሕይወታቸውም ኀልፈት በዚህ በሽታ ምክንያት ሲሆን ዕረፍታቸው በመጋቢት ወር መጀመርያ 1811ዓ.ም ነበር፡፡

አባ አብርሃም ባረፉ ጊዜ እርሳቸው ወደ አማርኛ የተረጐሙት መጽሐፍ ቅዱስ የእጅ ጽሑፍ በአስሊን እጅ በጥንቃቄ ተይዞ ነበር፡፡ በሜድትራንያን አካባቢ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ማኀበር ኃላፊ የነበረው ዊልያም ጆዌት በታኀሣሥ ወር 1804 ዓ.ም ወደ ግብፅ ሄዶ ከአስሊን ጋር በተገናኙ ጊዜ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ የትርጉም ሥራ ተጠናቅቆ ዐልቆ ነበር፡፡ አስሊንም ጆዌትን ባገኘው ጊዜ በአባ አብርሃም ከተተረጐመው ከፍተኛ ዋጋ ካለው ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የእጅ ጽሑፍ በከፊል ይዞ ራሱን አስተዋወቀ፡፡

መጽሐፉ በተርጓሚው በአባ አብርባም የእጅ ጽሑፍ 9539 ገጾች ነበሩት፡፡ የተጻፈውም በኢትዮጵያ የግዕዝ ፊደል ሲሆን እጅግ የተዋበና ተለይቶ የሚነበብ ቁም ጽሕፈት ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ማኀበርና የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር በአባ አብርሃም የእጅ ጽሕፈት ተመጣጣኝ ዋጋ እንጂ ሙሉ ዋጋ አልተጠየቍም፡፡ የጠየቁትም ዋጋ 1200 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ) ፓውንድ ብቻ ነበር፡፡ በአሁኑ ዋጋ ሲተመን ወደ 36,000.00 (ሠላሳ ስድስት ሺህ) የኢትዮጵያ ብር ያህል ነው፡፡ የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር በተጠየቀው ዋጋ ተስማማ፡፡ ወድያውም በታላቋ ብሪታንያ ውስጥ ባሉ የቋንቋ ባለሙያዎች ከተመረመረ በኋላ አራቱ ወንጌላት በ1816 ዓ.ም ታተሙ፤ ሐዲስ ኪዳኑም በሙሉ በ1821 ዓ.ም፣ መላው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በ1832 ዓ.ም ታተመ፡፡ አባ አብርሃም ተራው ሕዝብ በሚነጋገርበትና በሚያስተውለው የአማርኛ ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን በመተርጐማቸው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ታላቅ በረከትን አስገኝተዋል፡፡ ሕዝቡ በሚገባው ቀቋንቋ ቅዱሱን መጽሐፍ አንብቦ ምስጢረ ድኀነትን እንዲያውቅ አድርገዋል፡፡ በመሆኑም አባ አብርሃም ለኢትዮጵያ ክርስቲያን ሕዝብ ታላቅ ባለውለታ ናቸው፡፡ በተረጐሙት መጽሐፍ መግቢያ ስማቸው ሲወሳ ይኖራል፡፡ (ሐኪዳን አባ አብርሃም 1929)

መጋቢ ብሉይ ሰይፈሥላሴ ኢትዮጵያና መጽሐፍ ቅዱስ በሚለው መጽሔት ላይ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ካሳተመው መጽሔት የተወሰደ ነው፡፡

የኦሮምኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጒም ወለጋዊው የተከበሩ አናሲሞስ ነሲቡ (አባ ገመቺሳ) ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ኦሮምኛ ተርጒመዋል፡፡ እርሳቸው የትርጉም ሥራቸውን በሚሠሩበት ጊዜ ሰዊድናውያን አማካሪዎቻቸው ነበሩ፡፡ አስቴር ገኖም የቅርብ ረዳታቸው ነበሩ፡፡ ኦሮምኛው ሐዲስ ኪዳን በ1886 ዓ.ም ታትሞአል፡፡ የብሉይ ኪዳኑ የትርጒም ሥራ በ1890 ዓ.ም ተፈጽሞ በ1891 ዓ.ም ሙሉው የኦሮምኛ መጽሐፍ ቅዱስ ታትሞአል፡፡ የአናሲሞስ የሥራ ፍሬ የሆነው የኦሮምኛው መጽሐፍ ቅዱስ በአባ አብርሃም ትርጒምና በስዊድኖች መጽሐፍ ቅዱስ ትርጒም ተነጻጽሮአል፡፡

የትግረኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጒም

የትግረኛ መጽሐፍ ቅዱስ በተከበሩት አባት በአለቃ ተወልደ መድኀን ገብሩ ከ1861-1952 ዓ.ም ተተርጒሟል፡፡ አለቃ ተወልደ መድኀን ገብሩ በትግረ ውስጥ የማሚይሻም ተወላጅ ነበሩ፡፡ በትርጒም ሥራቸው ጊዜም ስዊድናዊት ዊንቅቪስት አማካሪያቸው እንደ ነበሩ ታውቋል፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ የትግረኛ ትርጒም በ1901 ዓ.ም ታትሞአል፡፡ ሙሉው የትግረኛ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በ1948 ዓ.ም ታትሞአል፡፡ አለቃ ተወልደ መድኀን ትግርኛ፣ ትግረ፣ ግዕዝ፣ አማርኛ፣ ዐረብኛ፣ ዕብራይስጥ፣ ጣልያንኛና ስዊድንኛ ያውቁ እንደ ነበር ዶ/ር ጉስታቭ አረን መስክረውላቸዋል፡፡

ከዚህም በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ በሌሎች የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር በተለያዩ ጊዜያት እየታተመ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በ1ኛው ሺህ ዓመት በግእዝ በሁለተኛው ሺሕ ዓመት በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግረኛና በሌሎችም የሀገር ቋንቋዎች የቅዱስ መጽሐፍን በረከት አግኝታለች፡፡ ይህ በረከት ሳይቋረጥ በሌሎችም ቋንቋዎች አማካኝነት እስከ ዕለተ ምጽአት ይቀጥላል፡፡

የተሻሻለው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጒም በ1923 ዓ.ም በቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ በኢትዮጵያ ሊቃውንት ብቻ ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተተረጐመ መጽሐፍ ቅዱስ ከ1928-1934 ዓ.ም ባሉት ዓመታት በሎንዶን በፎቶ ኦፍሴት ታተመ፡፡ መጽሐፉ በግዕዝና በአማርኛ ጎን ለጎን ስለተጻፈ ከትልቅነቱ የተነሣ በአራት ጥራዝ እንዲታተም ሆኗል፡፡ እንደ ገናም የካቲት 27 ቀን 1939 ዓ.ም ሰባት ኢትዮጵያውያንና ሦስት የውጭ ሀገር ሊቃውንት ያሉበት ጉባኤ በቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ትእዛዝ ተቋቁሞ በአባ አብርሃም የተተረጐመው መጽሐፍ ቅዱስ ከዕብራይስጥና ከፅርዕ ጋር በማነጻጸር የተሸሻለ ትርጉም አዘጋጅቶ በ1944 ዓ.ም አቀረበ፡፡ ምክንያቱም የአባ አብርሃም ትርጒም ቃል በቃል እንጂ የአማርኛ ሰዋስውን ሥርዐት የጠበቀ አልነበረም፡፡ ይኸው ትርጒም በ1953 ዓ.ም በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ታትሞአል፡፡ በዚህ ትርጒም ውስጥ በ1923 ዓ.ም ከግዕዝ ከተተረጐመው ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ.ክ የምትቀበላቸው ሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ተካትተዋል፡፡ ይኸውም የተሸሻለው ትርጒም በሐዲስ ኪዳኑ ላይ አንዳንድ እርማት ተደርጎለት በ1980 ዓ.ም ታትሞአል …

እንዚህ የተከበሩ አራት ቅዱሳን አበው አባ አብርሃም፣ አናሲሞስና፣ አስቴር ገኖ፣ አአለቃ “ተወልደ መድህን” ከፍተኛ የሀገሪቱ ክርስትና አንቀሳቃሽ ነበሩ ብንል አንሳሳትም፡፡ እንዳውም እንደኔ እንደኔ መታሰቢያ ሐውልት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በታሪክ አሻራነት ለሚመጣው ትውልድ መታየት አለባቸውና፡፡ እነዚህ አባቶች በማቴሪያልም፣ በገንዘብም፣ በመሠረታዊ ነገሮች ቢረዱም ለዓመታት ቁጭ ብለው የታያቸውን ብርሃን እኛ እንዲታየን አድርገዋል፡፡ እግዚአብሔርን ስለ እነርሱ ስናመሰግን እነዚህን ሰዎች ያሳደገች ቤ/ክ አባቶችና የረዷቸው ቅዱሳን ትውልዳቸው የተባረከ ይሁን! ለማለት እንደፍራለን፡፡

የተወደዳችሁ ወገኖች በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በአምስት የሀገራችን ቋንቋዎች ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን እያቀረበልን ነው።ወደ 25 ቋንቋ ደግሞ አዲስ ኪዳን ይኖራል።ገና 30 ቋንቋ ይቀራል።መከሩ ደግሞ ብዙ ነው በዚህ የመከር ሥራ መሳተፍ በጣም ያስፈልጋል።በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ መጽሐፍ ቅዱስ እያነበበ ሰባኪ የሰበከውንም እውነት ይሆንን? እያለ የሚጠይቅበት ደረጃ ስለደረሰ መጽሐፍ ቅዱስ በጣም ስለሚፈልጉ እጥረት ይታያል።ወደ ሀገራች ደግሞ ማተሚያ እንዲገባ እግዚአብሔር እንዲረዳን የምንለምንበት ጊዜ አሁን ነው።ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምን።

ታላላቅ ሰዎች ስለመጽሐፍ ቅዱስ ምን ብለው ነበር?

1= የመጽሐፍ ቅዱስ ግልጥነት እንደ ተንጣለለው ሰማይ ነው።ግዙፉም እንደውቅያኖስ ጥልቅነት ነው፤የሚያንጸባርቅ ትርዒቶቹም እንደ ሥነፍጥረት ናቸው።

እንግሊዛዊው ጆን ሄንሪ ኒው ማን ክርስቲያናዊ ሰባኪ

2= በየዘመኑ ሁሉ በሚደረገው አዕምሮአዊ ዕድገት መጠን እንደዚሁም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጎ የትምህርት ማሳተፊያ ማድረግ ማለት ግድ የለሾችን ወይም ችላ ባዮችን ማለቴ ሳይሆን በእውነተኛ ጉዳይ ብልሆችን ለማዘጋጀት የሚቻልበት መንገድ ነው።

ጀርመናዊ ባለቅኔ ጉይት

3= ጌታ ሆይ መጽሐፍ ቅዱስ ሪፕብሊካዊት መንግሥታችን የተመሰረተበት ማለት ነው።

አሜሪካዊ ፕሬዝዳንት አንድሪው ጃክሰን

4= የእንግሊዝ አገር ታላቅነትም ምስጢሩ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

እንግሊዛዊት ቪክቶሪያ

5= ያለ እግዚአብሔርና የእግዚአብሔር ቃል ከሆነው ያለ መጽሐፍ ቅዱስ ዓለምን ማስተዳደር በፍጹም የማይቻል ነው።

አሜሪካዊው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን

6= ቅዱሳት መጻሕፍት በሚያስተምሩት መሠረታውያን ቁም ነገሮች የጸናን እንደሆነ ሀገራችን ሥልጣኔዋን እያዳበረች ትሄዳለች።እኛና ተከታዩ ትውልድ የቅዱሳት መጻሕፍትን ትምህርቶችና ኃይለ ቃል ሁሉ ችላ ያልን እንደሆነ ግን አንድ ድንገተኛ መዓት

የሚደርስብንና ክብራችንንም ከትቢያ ጋር የሚለውሰው ለመሆኑ ምንም መናገር አይቻልም።

ዳንኤል ዌብሰተር

7= መጽሐፍ ቅዱስ ሆይ፣ባነበብኩህ ቁጥር አንዲት ኃጢያት ታስተርይልኛለህ፤ ወይም ኃጢያትን እቋቋም ዘንድ የቅድስና ጎሃ በልቤ ታሳድርልኛለሁ።>

ታላቁ የእንግሊዝ ደራሲ አይዛክ ዎልተን

የእግዚአብሔር ቃል ማለት ብሉይ ኪዳን፣ የእግዚአብሔር ሕግ፣ የሙሴ ሕግ፣ የኦሪት ሕግ፣ ቶራ፣ታልሙድ፤ ሰፕቱዋጅንት በመሳሰሉት ስም እየተጠራ እዚህ ዘመን ደርሷል፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚያስተዳድርበትን ሕግ በድንጋይ ጽላት ቀርጾ መስጠቱ እግዚአብሔር በጽሑፍ ጉዳይ ላይ ጠንከር ያለ ነገር እንዳለው በአንድ በኩል ስናይ በሌላ በኩል ደግሞ የጽሑፍ ጉዳይ ለእግዚአብሔርም ትልቅ አጀንዳው እንደሆነ እናስባለን፡፡ (ዘፀ፣20) በቀድሞ ዘመን የተነሡት መንፈሳዊያን መሪዎች እግዚአብሔር እየረዳቸው ቃሉን በመጻፍና በማስቀመጥ ዐደራቸውን እየተወጡ ዐልፈዋል፡፡ በፖፒረስ ወረቀት፣ በድንጋይና በብራና ላይ የእግዚአብሔር ቃል እየተጻፈ ለትውልድ ተላልፎአል፡፡ የሙት ባሕር ጥቅል መጽሐፎች (Dead sea scrolls) በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በተቃኙ ሰዎች ተሰብስበውና ተመርምረው ዋና መረጃ ሆነዋል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆኑ ተረጋግጠውም ለእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲደርሱ ተደርገዋል፡፡ ከዚያም ወዲህ በየዘመናቱ የተነሡት ትውልዶች ቃሉን በዐደራ ተረክበው ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ በመጀመሪያ ጊዜ በምንም ዓይነት መንገድ ቃሉ እንዳይተላለፍ የቃሉ ባለዐደራ የነበሩትን የአይሁድ ትውልዶች ለማጥፋት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡ ትውልዱ ደግሞ ሳይጠፋ ሲቀር በየጊዜው የተጻፉባቸውን ድንጋዮች አድቅቆ በመፍጨት፣ ፓፒረሶችን በማጥፋት፣ ብራናዎችን በውሃ በማጠብ የተለያዩ ሙከራዎች ተካሂደዋል፡፡ ሆኖም ቃለ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር ጉልበትና ችሎታ እያሸነፈ ዛሬ ድረስ ደርሶል፡፡ በርናርድ ራም የተባለ ሰው ሺህ ጊዜ መጽሐፉ እንደሞተ ተለፍፏል፣ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ተካሂዷል፣ መቃብሩ ላይ ማስታወሻ ተጽፏል የሕይወት ታሪኩ ተነቧል ዳሩ ግን ሬሳው ጉድጓድ ውስጥ ቆይቶ አያውቅም፡፡ በማለት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጽፏል (ድንቅ መጽሐፍ ከሚባለው የተወሰደ)፡፡

በዕብራይስጥ በግሪክና በላቲን ቋንቋዎች በስፋት የተጻፈው ሕገ እግዚአብሔር በተለይ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ለእኛ ትውልድ በገነነ መልኩ እንዲታወቅ የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነው እየተባለና በዘመናዊ ማተሚያ ቤቶች እየታተመ ስሙን በሥልጣን በማስጠራት ለትውልዳችን ደርሷል፡፡

በየዘመናቱ የቃሉ ዕውቀት አለን የሚሉ፣ ያነበቡ፣ ከአእምሮቸው ግን ወደታች ያልወረደና ያልተዋሐዳቸው ትውልዶችና መሪዎች ቃሉን በማጣመምና እንደሚፈልጉት በመተርጐም እግዚአብሔርን በመፈለግ የተጠማውን ሕዝብ ሲያስቱት ያየ እግዚአብሔር “ቃሉ” ለሕዝብ ሁሉ እንዲገባ በተለይ “ተራ” የተባለው ሕዝብ መረዳት እንዲያገኝ የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅሟል፡፡ “ትምህርተ እግዚአብሔር” በተባለው ቄስ ማንስል ኮሊን ባዘጋጁት መጽሐፍ ላይ “ከዐምስት ሺህ በላይ በግሪክ ቋንቋ በእጅ የተጻፉ የዐዲስ ኪዳን ቅጅዎች አሉ የመጀመሪያዎቹ ቅጂዎች በ135 ዓ.ም ገደማ እንደተጻፉ ይታሰባል፤ በጠቅላላው ዐዲስ ኪዳን ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተገኘ ሲሆን በላቲን የጀሮም ትርጒም፣ አንዱ ነው ይህም ቩልጌት በመባል ይታወቃል፡፡ ከዚህም ጋር ልዩ ልዩ አንቀጾች በሁለት ሺህ የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍተ ጸሎት ተገልብጠዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባቶችም ከሰማንያ ስድስት ሺህ ጊዜያት በላይ ዐዲስ ኪዳንን በጽሑፎች ጠቅሰውታል፡፡ ሊቃውንት ይህንን ሲመረምሩ የዐዲስ ኪዳን የመጀመሪያ ረቂቆች ምን እንደሚሉ ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት የጥንት ቅጂዎችን በመመርመራቸው ትክክለኛ የዕብራይስጥና የግሪክ ረቂቆች ምን አሳብ እንዳላቸው አረጋግጠዋልና ትልቅ አገልግሎት ፈጽመዋል፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔርን ማመስገን ይገባናል ብለዋል፡፡ ታዲያ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ሁሉ ሊያነቡት በሚችሉት ቋንቋ መተርጐሙንና ሰዎች ቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር በቃሉ አማካይነት ሊነጋገሩ ይገባል የሚለውን መርሕ ተግባራዊ በማድረግ “የንጋቱ ኮከብ” ወይም “The moring star” ተብሎ የሚጠራው በ1312 የተወለደውና በ14ኛው ክፍለ ዘመን ለአገልግሎት የተነሣው የእንግሊዝ ሀገር ተወላጅ የሆነው ዮሐንስ ዊከሊፍ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በዘመኑ የማይደፈረውን በመድፈር “ከላቲን ቩልጌት” ወደ እንግሊዝኛ ተርጒሞ በማበርከቱ መጽሐፍ ቅዱስ በሕዝብ መነጋገሪያ ቋንቋ ሊቀርብ እንደሚገባው አሳማኝና ቀስቃሽ መልክትን አስተላልፎአል፡፡ ዮሐንስ ዊክሊፍ ሰው ሊገባው በሚችል ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ መተርጐሙና ዕድሉ ያላቸው ሁሉ ማንበባቸው በዘመኑ በነበሩት የሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ተቃውሞ አስነሥቶበት ነበር፡፡ ዊክሊፍ ከዚህ ዓለም ከተሰናበተ በኋላ፣ ያነበቡት ሰዎች እንዳነበብነው እንኑር፣ መስተካከል የሚገባው ይስተካከልልን በማለታቸው የተበሳጩ የቤ/ክርስቲያን መሪዎች ንዴታቸውን በበቀል የተወጡት በዊክሊፍ “ዐፅም” ላይ ነበር፤ ይኸውም የዊክሊፍ ዐፅም ከ31 ዓመት በኋላ ተቆፍሮ ወጥቶ፣ ተከስክሶ፣ ደቆ ተፈጭቶ ወደ ባሕር እንዲበተን በማድረግ ነበር፡፡

ከእርሱ ቀጥሎ የተነሣው ዮሐንስ ሁስም የዊክሊፍን ዐላማ በመከተሉ “እስከሚያነበው የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ በዕንጨት ላይ ታስሮ እንዲቃጠል ተደርጓል” ይህ ትርጒም በተለያዩ ሰዎች ከዚያ በኋላ ተነቧል፤ ለምሳሌ ሊገባው በሚችለው ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ የተረዳውና ሕይወቱ ያደረገው ዕውቁ ሰባኪ በ1795 የተወለደው ጆን ዌስሊ ደግሞ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር “አንድ ነገር ብቻ ላውቅ እወዳለሁ! እሱም ወደ ሰማይ የሚመራ መንገድ ሆኖ በዚያ ደስታን በተሞላ ዳርቻ ያለምንም ሥጋት ለማረፍ ነው፤ እግዚአብሔር መንገዱን አብራርቶ በመግለጥ ሰውን ሁሉ ለማስተማር ፈቅዶአል፤ በአንድ መጽሐፍ አጠቃሎ አስመዝግቦታል፡፡ ያንን መጽሐፍ ስጡኝ፣ በማናቸውም ዋጋ ቢሆን ያንን መጽሐፍ ስጡኝ፣ አገኘሁት፡፡ እዚህ ለኔ የሚበቃ ዕውቀት አለልኝ፣ ብቻ ባለ አንድ መጽሐፍ ልሁን” ብሎአል፤ በዚህ የሲቃ ንግግሩ ለመጽሐፍ ቅዱስ ማለትም ለቃሉ ያለውን ፍቅር አሳይቶአል፡፡

የቃለ እግዚአብሔር ትርጒም እንዲህ እየሰፋ በዘመኑ ያለው ሕዝብ ሊደርሰው በሚችል ቋንቋ መሆን አለበት በሚል መርሕ የተጀመረው ይህ ሥራ “ብዙ ዋጋ ተከፍሎበት ነው የቅዱሳን ዐጥንት ደቅቆ፣ ተፈጭቶ፣ ሥጋቸውም በእሳት ተቀዋጥሎ ነው እዚህ የደረሰው ማለት ይቻላል” ዛሬ በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጒሞ ሲገኝ ያለፈውን ታሪክ ያላወቀ ትውልድ እንደ ቀላል በማየት እግዚአብሔርን ላያመሰግን ይችላል፡፡ የዚህ ጒድለት እኛ ቀደም ብለን ይህንን ያወቅን እግዚአብሔር በቃሉ እንዲህ ብሎ ያዘዘንን ስላላደረግን ይመስለኛል “እግዚአብሔር ያደረገላችሁን ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ንገሯቸው” በተባለው መሠረት ታሪክን መናገር የወላጆችና የአባቶች ኃላፊነት ነው፣ ይህ ደግሞ የሚጠቅመው እግዚአብሔር የሰጠንን ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ማቴሪያል በወጉ እንድንጠቀምበት ይረዳናል፡፡ ለምሳሌ፡- በ305ዓ.ም የተነሣው “ዲዮቅልጥያኖስ (DIOCLETION)” አብያተ ክርስቲያናት ይዘጉ፣ አብያተ ጣኦታት ይከፈቱ በማለት ሲያውጅ በየጊዜው የተገኙ መጽሐፍ ቅዱሶች እንዲቃጠሉ አድርጓል፡፡ በመቀጠልም ድሉን ለማክበር ሲል ባቃጠላቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ታላቅ ዐምድ አቁሞ ቢዘባበትም በአንጻሩ ከ 25 ዓመት በኋላ የዐዲሱ ንጉሥና ንግሥት ዕሌኒ ልጅ ቆስጠንጢኖስ “አብያተ ጣኦታት ይዘጉ፣

አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ ብሎ ዐዋጁን በመመለስ ብዛታቸው 50 የሚሆን መጽሐፍ ቅዱሶች በራሱ ወጭ እንዲጻፉ አድርጓል” (መጽሐፍ ቅዱስና የሕክምና ሳይንስ በ2004 ዓ.ም ከሚለው የተወሰደ፡፡

ታድያ ወደ ሀገራችን ስንመጣና የታሪክ መዛግብቶችን ስናገላብጥ የቃለ እግዚአብሔር ትርጒም በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ክርስቲያን ጳጳስ በሆኑት በአባ ፍሬምንጦስ ከግሪክ ወደ ግዕዝ ትርጒም እንደ ተጀመረና ወደ ሀገራችን በተለያየ ምክንያት ፈልሰው የመጡት ዘጠኙ ቅዱሳን የግዕዙን ትርጒም እንደ አጠናቀቁ ታውቋል፡፡ በየመሠረቷቸው ገዳማትም የግዕዝ ቅዱሳን መጻሕፍት እንደ ነበሩ መረጃዎች አሉ፡፡ በተለይ እነዚህ መነኮሳት በዘመኑ ለእግዚአብሔር ቃል መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረጋቸው ለኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ባለውለታ ናቸው፡፡

በዘመኑ አብዛኛው ሕዝብ ግዕዝ ይናገራል፤ ይጽፋል፤ ስለዚህ በግዕዝ የሚነበበውም “ቃለ እግዚአብሔር” ይገባው ነበር፡፡ በኋላ ኋላ ግን ቋንቋው ከቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ጋር ብቻ በመቅረቱ ነገሮች እንደ ታሰበው አልሄዱም፤ ሆኖም ከዚህ ውስጥ እግዚአብሔር አንድ ታሪካዊ ነገር አወጣ ! ምን?እንደእነ አባ አብርሃም እንደነ የተከበሩትን አናሲሞስንና አስቴር ገኖን እንደነ አለቃ ተወልደመድህን ያሉትን ቀደም በማለት የዘረዘርናቸውን ልናሳውቃችሁ ሞክረናል።

በአሁኑ ጊዜ በተደረገው ጥናት የ SIL የትርጒም አማካሪና ዳይሬክተር በአንድ ሴሚናር ላይ እንደ ገለጹት በኢትዮጵያ 33.1 ሚሊዩን ሕዝቦች ያለ መጽሐፍ ቅዱስ ይገኛሉ፡፡ በቋንቋቸው አልተተረጐመላቸውም፡፡ 35 ቋንቋዎች ፊደል የላቸውም፣ አንድም ጥቅስ ገና የላቸውም፣ ምናልበናትም በቁጥር እነዚህ ቢገመቱ 3.5 ሕዝቦቻችን ናቸው፤ እንግዲህ በ5 ቋንቋ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ፣ በ18 ቋንቋ ዐዲስ ኪዳን ያገኘው ሕዝባችን የታደለ ሆኖ እግዚአብሔርን ስናመሰግንና ስናከብር ለዚህ የተጋደሉልንንም እንባርካለን፡፡ ሆኖም 23 ቋንቋዎች ገና በሥራ ላይ ያሉ ወይም በትርጒም ሂደት ያሉ ናቸው፣ 22 ቋንቋዎች በበጀት ያለመገኘት ገና ምንም የትርጒም ሥራ ያልተጀመረላቸው ናቸው፡፡ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ጠቅላይ ጸሐፊ እንደገለጹት አንድን መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ ለመተርጎም 2ሚሊዮን ብር ገደማ ሲፈጅ በትንሹ 10 ዓመት የጊዜ ገደብ ያስፈልገዋል። ዛሬ እግዚአብሔር ረድቶን በሀገራችን የሃይማኖት፣ የቋንቋ፣ የባህል ልዩነት ሳይኖር በእኩልነትና በሰላማዊ መንገድ እግዚአብሔር በሰጠን፣ መንግሥትም በከፈተልን ዕድል መብትን ለመጠቀም ጊዜው አሁን በመሆኑ፣ ታሪክ የሚጠይቀንን ሥራ ለእግዚአብሔር መንግሥት፣ እንደዚሁም ለሕዝባችን ፈውስ ሊያመጣ በሚችለው በቃሉ ላይ መትጋት ይኖርብናል፤አብያተ ክርስቲያናት ስለ ወንጌል ፍቅርና ስለ አንዲት ነፍስ መዳንና ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መቀላቀል ስንልስ ለእነዚህ ሕዝቦች መዳን መጋደል አንችልም ወይ?

ለእኔ ቃሉን ማዳረስ ወይም ማሠራጨት ማለት “መንገዱን መጥረግ ነው፡፡” ቃሉን የሚያደርሱ ሰዎች ወይም አብያተ ክርስቲያናት ወይም ድርጅቶች ጌታ እንዲመጣና መንፈስ ቅዱስ ሥራውን እንዲሠራ መንገዱን መጥረጋቸው ነውና፡፡ ለዚህም ከታሪክ የምንማረው አንድ አስገራሚ ነገር አለ፡፡ “መፈለግንና ማድረግን በውስጣችሁ የሚያደርግ እግዚአብሔር ነውና” እነደሚል ቃሉ (ፊል.2፣13) የቃሉ ጥማት ዕረፍተቢስ የመሆን ነገር ያሳደረባትን የሜሪጆይስን ታሪክ በመጠኑ ልናውቅ ይገባል፡፡ ዛሬ ላይ ቆመን ነገሩን ወደ ኋላ ሄደን ካላየነው እንደ ቀላል በማየት ምስጋናን ለእግዚአብሔር እንዳንነፍግ ይረዳናል፡፡

እግዚአብሔር ዓለምን ያንቀሳቀሰ ሥራ በሜሪ ጆንሰን ሠርቷል፡፡ ለእርሷ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ነፍስ መትረፍ ምክንያት አድርጓት በጉዳዩ አጣዳፊ እርምጃ እንዲወሰድ ክርስቲያኖችን አነሳሥቶአል፡፡ የማይዘገየው እግዚአብሔር ሊቀደም አይችልምና ነው፡፡ ሜሪ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ፍለጋ በእግርዋ የተጓዘችው 40 ኪሎ ሜትር ያህል ነው፡፡ ለ6 ዓመት ሠርታ ያጠራቀመችውን ገንዘብ ቋጥራ በ16 ዓመትዋ ይህነን አድካሚ የእግር ጉዞ አድርጋለች፡፡ በዊከፒዲያ ላይ እንዳየሁት በ8 ዓመት ዕድሜዋ ነበር ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የተነገራት፡፡

መጽሐፍ ቅዱሱን የግሏ ለማድረግ፣ ከውሰት ለመውጣት፣ ሌሎች ብቻ ሲያነቡት ከመስማት ራስዋ ለማንበብ ቆርጣ የተነሣችው ሜሪ የገበሬ ቤተሰብ የነበረች ብትሆንም ድህነት ያሳደረባትን ተጽዕኖ ሰብራ በመውጣት ራስዋን ከመሃይምነት አላቀቀች፡፡ የሜሪ ፍላጎት የተሟላው በመሥዋዕትነት ነበር፡፡ ታዲያ ሜሪ በወቅቱ መጽሐፍ ቅዱሱን በሸጠላት በካህኑ አእምሮ አንድ ነገር ጭራ ዐለፈች፤ ለካ እንደ ሜሪ መጽሐፍ ቅዱስ የሚፈልጉ በየአካባቢው አሉ በማለት በለንደን ለተሰበሰበው የካህናት ጉባኤ እባካችሁ እናስብበት ብለው አቀረቡ፡፡ ጉባኤውም ታድያ ይህንንማ ለምን በዌልስና በለንደን ብቻ ብሎ ተገቢውን የመፍትሔ እርምጃ ይወስድ ዘንድ በመጋቢት 15/1796 ዓ.ም በለንደን “የብሪቲሽና የውጭ ሀገር የመጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር” የሚል ተመሠረተ፡፡ እንግዲህ ይህ ማኀበር ነው ለሌሎቹ ሁሉ መሠረት በመጣል ለካ ይቻላል የሚልን መነሣሣት በወቅቱ ያሳየው የሚል እምነት አለኝ፡፡

ታዲያ ሳይታሰብ የአባ አብርሃም የትርጒም ሥራ ታትሞ በመርከብ ወይም ከ5 ሺኪ.ሜ በላይ የአውሮፕላን በረራ ከሚደረግበት ወይም የዛሬው ዘመናዊ በረራ ካለበት ለንደን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እኛ ዘንድ ደረሰ፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ወደ እኛ እንዲደርስ እግዚአብሔር ምክንያት አድርጎ በወቅቱ የተጠቀመባት ይህች ብላቴና አንቱታ የሚቸራት ናት ሚስ ጆይስ ሜሪ የከፈለችውን ዋጋ ዛሬ ላይ ቆመን ስናስብ ለዚያ ዘመን ቀላል አልነበረም፡፡ አንድ አሻራ ትታልን እንዳለፈች ግልጽ ነው፡፡ የተቆለፈበት ቁልፍ የሚለው በዶ/ር ምሕረት በተጻፈው መጽሐፍ ላይ እንዲህ አነበብኩ፣ በየትኛውም አቅጣጫ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ሰዎች የተለያየ ስም ቢሰጣቸውም፣ እነዚህ ጥቂት ብርቅዬ ከዋክብት ከኀብረተሰቡ በ30 እና በ40 ዓመት ቀድመው ወደፊት የሄዱ ስለሆነ ከሰው አይገጥሙም ይሉናል፡፡ ገጽ81፡፡

ዛሬ የተከበሩትን አባት የአባ አብርሃምን ገድል ስናነብ ወይም ስንሰማ እንደ ቀላል ነገር ካልቆጠርነው ለ10 ዓመታት ያህል አንድ ቦታ በመቀመጥ ለተሰጡለት ትርጒም በውስጣቸው የታያቸውን ስንረዳ፣ በዘመናቸው ባገኙት መነጽር ዛሬ ላይ ቆመው እኔንና እናንተን እንዳዩ፣ ከጎናቸው የነበረውም ፈረንሳዊው አስሊንም ከፈረንሳይ ግብፅ ገብቶ እኔንና ሕዝቤን እንዳየ አልጠራጠርም፡፡ ዛሬ በቀላሉ ተጠርዞ እጃችን ስለ ገባ ማየት ከተሳነን በደለኛ አንሆን ይሆንን? ይህን ያልኩት ዛሬ ሚሊዮኖች ይህ ቃል ያስፈልገናል ወደ ማለት ዘመን ላይ ደርሰናልና ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ዛሬ ካለው የኑሮ ተግዳሮት አኳያ ዐቅም ዐጥተው መግዛት ያልቻሉ በሚሊዮኖች ናቸው ስላችሁ ማጋነን እንደ ማይመስላችሁ አስባለሁ! ይህንን ለማረጋገጥ ወደ ማኀበሩ ጽሕፈት ቤት ጠጋ ማለት ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ፤- የዛሬ 5 ዓመት ጠቅላይ ፀሐፊው ባቀረቡት ገለጻ ላይ በአንድ በሀገራችን ባለ እስር ቤት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የሶስቱ ሥላሴ አማኞች እየተዋዋሱ ሲያነቡ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ቅዳሴያቸው በሌሊት ስለሆነ በዚያ ሰዓት አንብበው ከጨረሱ በኋላ ለካቶሊክ አማኞች ይልካሉ፤ ካቶሊኮች ረፈድፈድ አድርገው የጀመሩትን ቅዳሴ ሲጨርሱ አንብበው ከሰዓት በኋላ ለሚያመልኩት ለወንጌላውያን ይልካሉ፡፡ ይህ በግልጽ የታየና የሚታወቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ይህን ይጥቀሱት እንጂ እኛም በምናደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ነጻ የሥርጭት አገልግሎት አልዳረስ እያለን በየክልሉ የገጠመን ተግዳሮት ቀላል አይደለም፡፡ የ30 ሺመጽሐፍ ቅዱስ ሥርጭት ስናደርግ የ63 ሺው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ በጽሕፈት ቤታችን እንዳለ ተቀምጧል፡፡

ሌላ የማንክደው ሐቅ መጽሐፍ ቅዱስ ከእንግሊዝ ሀገር ታትሞ ሲመጣ በመጀመሪያ ይዞ የገባውና በሀገራችን ለማስተዋወቅ የሞከረው የምሥራቅና የሰሜን አፍሪካው የሚሲዮናውያን ተልእኮ ክፍል ነው፡፡ በደረስኩበት መረጃ መጽሐፍ ቅዱስ የእኛ አይደለም የሚሲዮን ነው መባሉ ወይም ሌላ ስም እንዲሰጠው ያደረገው ይህ የቀረበበት መንገድ ነው፤ ከዚህ መረጃ ግዕዙን የተቀበለው ክፍል አማርኛወን አልቀበልም ቢል አያስደንቅም፤ አባ አብርሃም የቤ/ክርስቲያኒቱ ብርቅዬ ልጅ ይህንን ሥራ እንዴት ደክመው ዋጋ ከፍለው እዚህ እንዳደረሱት እንኳን ከመጽሐፍ ቅዱሱ ርቆ ይሆናል የምንለው ሕዝባችን ቀርቶ በእጁ መጽሐፉ ያለውም የተረዳው ስንቱ እንደሆነ የአብያተክርስቲያናት መሪዎች ያውቁታል፡፡ ይህንን ግን ሕዝባችን ቢያውቅ ኑሮ ከበረከቱ ለመካፈል ቀዳሚ በሆነ ነበር፡፡ ሆኖም አሁን ከዚህ መረዳት እየወጣ ነውና ለዚህ መውጣቱ እግዚአብሔርን ስናመሰግን ግን አቅርቦቱን በሚመለከት ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ኀላፊነት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ክርስቲያን ግለሰብ፤ ቤተሰብና ቤ/ክርስቲያን ኃላፊነት ነው፡፡ አንድ ነገር ሲደጋገም ባህል ሆኖ ያስቸግራል፣ መልካም ነገርም ቢሆን ሲደጋገም ነውና እንዲህ የሚሆነው እነዚያ ሚሲዮናውያን ወደ ሀገራችን ሲገቡ ሰው እንዲለምድላቻው መጽሐፍ ቅዱስን በነጻ ይሰጡ እንደ ነበር መረጃዎች አሉ፡፡ ይህ የማይካድ ሐቅ ነው፣ ታዲያ ዛሬም ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር የመሸጫ ሱቆች ወይም ዋና ጽሕፈት ቤት ጎራ በማለት መጽሐፍ ቅዱስ በነጻ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ እንዳሉና እንዲያውም እንዴት ትሸጣላችሁ? የእግዚአብሔር ቃል ይሸጣል እንዴ? በማለት ቁጣ አዘል ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ ምነው ገንዘቡ ኖሮን ገዝተን ለሚፈልጉት ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ፣ በነጻ ለመስጠት ዕድሉን ባገኘን ያሰኛል፡፡ አሁንም እኮ የሚታተምበትና የሚሸጥበት ዋጋ ተመጣጣኝ ሆኖ አይደለም፣ የዛሬ ዓመት ዘገባ እንደሚለው አሳትሞ ሀገር ውስጥ ለማስገባት 110 ብር ገደማ ሲደርስ የሚሸጠው ግን ከ65 እስከ 75 ብር ነበር፤ ዛሬ ግን ዋጋው ጨምሯል፡፡

የዓለምን ኤኮኖሚ ሁኔታ መረዳቱ ካለን ዋጋው አይገርመንም፤ ታዲያ የውጭዎቹ ማሳተሚያ ገንዘብ ሰብስበው አሳትመው ልከውልን እንደገና ደግሞ ለመግዛት እንድንችል ማካካሻ? REMBERECEMNET አድርገውልን እስከመቼ ነው የምንዘልቀው ? ባለ 85 ወይም 90 ሚሊዮን ሀገር ሕዝብ እንደሆን መዘንጋት የለብንም፡፡ በዓመት 500ሺ እንኳን ቢገባ ይጠቅመናል ወይ ትውልዱን ለመታደግና መጽሐፍ ቅዱስ ለሚመጣው ትውልድ ለማድረስ በዛሬ መነጽር ነገን ማየት ብንችል፤ መልካም ይሆናል፡፡ መጽሐፉ በእጃቸው ከደረሰ ክርስትናም የጠበቀ ወይም የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ቃሉ በወቅቱ ያልደረሰላቸው በቃል ብቻ ከሌሎች የሰሙትና በቃላቸው ለመያዝ የሞከሩት የሰሜን አፍሪካ ሀገሮች አንዱ የተጠቁት በዚህ መሆኑን ትምህርተ እግዚአብሔርን የጻፉት፣ የሀገራችን የኢትዮጵያና የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ወዳጅ የነበሩትና ወደ ጌታ የተሰበሰቡት ቄስ ማንስል ኮሊን አስፍረውታል፡፡ “መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት እየለወጠ አናኗራቸውን ከክፋት ነገር ወደ መልካም ለመለወጥ ታሪካዊ እንደ ሆነና መለኮታዊ ነገር እንዳለው ታውቋል” በኑቢያ (በሱዳንና) በሰሜን አፍሪካ ብዙ ሕዝቦች ወንጌልን ተቀብለው ነበር፡፡ ነገር ግን በ600 እና በ1200 ዓ.ም መካከል በዚያ አካባቢ ያሉ ሰዎች ሁሉ ማለት የክርስትና ሃይማኖትን ክደዋል፡፡ ከምክንያቱ አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ሕዝቦች ቋንቋዎች አለመተርጓሙ ነበር፡፡ ካሉ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ በሕዝብ ቋንቋ ተተርጉሞ ከተገኘ የማንኛውም ቤ.ክ ትልቅ ሀብት ነው፡፡

ታዲያ መቶ በመቶ በማዳረሱ ሥራ ባትያዝም፣ ቤተ ክርስቲያን ከወንጌል ሥርጭት ጐን የመጽሐፍ ቅዱስ ሥርጭት ክፍል ሊኖራት አይገባም ወይ? ከ85 ሚሊዮን እስከ 90 ሚሊዮን ለሚደርስ ሕዝብ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት በውጭ እያሳተሙ አስገብቶ ማዳረስ ይቻላል ? ለምን ማተሚያ ቤት በሀገራችን አይኖርም? 45 ሚሊዮን ኦርቶዶክሳውያን፣ ግማሽ ሚሊዮን የካቶሊክ እምነት ተከታዮች፣ 20ሚሊዮን የወንጌላውያን አማኞች ባሉባትና ወንጌል ያልተሰበከላቸው ገና ሚሊዮኖች ይኖራሉ በምንልባት ሀገር እንዴት መጽሐፍ ቅዱስ ከውጭ እናስገባለን ? መልስ ያስፈልገዋል፣ አቋምም ያስፈልገዋል፡፡

ከላይ እንደገለጽኩት አንድ ገጠመኝን ላሳያችሁ፤ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትውልድ ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለው አመለካከት ምን ይመስላል ? ስንቱ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ በእጁ አለ? ስንት አብያተ ክርስቲያናት፣ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ትውልድ እጅ እንዲገባ እያደረጉ ነው? ይህ ጉዳይ አነጋጋሪ ነው፡፡

ዛሬ ያለው ትውልድ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከሞባይል ማን ይበልጣል? ተብሎ ቢጠየቅ ማን ይበልጣል የሚል ይመስላችል? (መጽሐፍ ቅዱስ የሚጭኑትን ስልኮች አይመለከትም) በአንድ ክልል በሚገኘው የወንጌላውያን ቤ/ክ መጽሐፍ ቅዱስ ለሌላቸው በነጻ እንሰጣለን ብለን ለመሪዎች ነግረን መሪዎች መግዛት የማይቸሉትን መርጠው አመጧቸው፡፡ በሰልፍ ሆነው እየፈረሙ ሲወስዱ “ሞባይል” ይዘዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ግን የላቸውም! ታዲያ ይህን ምን እንለዋለን? ዛሬ ዕለት ዕለት ቃሉን በማንበብ የሚጠቀሙ ስንቶች ናቸው? መጽሐፍ ቅዱስ ከማንኛውም ነገር የበለጠ ዋና የክርስቲያን መመሪያ እንደሆነ አበክሮ ማስተዋወቅ ሳይጠበቅብን ይቀራል? እንደውም አልፎ ተርፎ እኮ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይዙ ወደ ቤ/ክ የሚመጡትን ለማወቅ ነገ እሁድ የሚሰበሰቡትን ምእመናን ብትጠይቁ ትገረሙ ይሆናል፡፡ ለእኔ አንድ ሰው እንኳን ይዞ ባይመጣ ያስገርመኛል፤ ያውም በወንጌላውያን መካከል ማለት ነው፡፡ የምለው ይገባችኋል፡፡

ቃሉን ወዳጅ አድርጎ ማሰላሰል፣ ማብላላት፣ የቃሉን ምስጢር የምንረዳበት መንገድ እኮ ነው፡፡ የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ አይደለም እንዴ የሚለው?

Anim pariatur cliche reprehenderit, enim eiusmod high life accusamus terry richardson ad squid. 3 wolf moon officia aute, non cupidatat skateboard dolor brunch. Food truck quinoa nesciunt laborum eiusmod. Brunch 3 wolf moon tempor, sunt aliqua put a bird on it squid single-origin coffee nulla assumenda shoreditch et. Nihil anim keffiyeh helvetica, craft beer labore wes anderson cred nesciunt sapiente ea proident. Ad vegan excepteur butcher vice lomo. Leggings occaecat craft beer farm-to-table, raw denim aesthetic synth nesciunt you probably haven't heard of them accusamus labore sustainable VHS.

መጽሐፍ ቅዱስን ለመንፈሳዊ ነገር ብቻ የሚጠቅም አድርጎ ማሰብ በሀገራችን ሊቀረፍ የሚገባው ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለማያምኑት እንኳን ቢሆን የጥበብ ምንጭ፣ ምክር አፍላቂ፣ ቀና ጎዳናን ለማሳየት የሚጠቅም፣ ለሳይንስ ምርምር እንኳ የሚረዳ ብቸኛ መጽሐፍ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ቀድሞ በትምህርት ቤት የግብረገብ ትምህርት ሲሰጥ አስታውሳለሁ፡፡ ዐሥርቱን ትዕዛዝ የሚያስተምሩን አባት ከመጽሐፍ ቅዱስ ነበር፡፡ ያ ትምህርት ታዲያ ፈሪሃ እግዚአብሔርን አሳድሮብን ለዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር እንዳበቃን አልጠራጠርም፡፡

በአሁኑ ዘመን ላለው ሳይንስ መሠረት የጣሉ ብዙዎች ጠበብት መጽሐፍ ቅዱስን ዘወትር የሚያነቡ እንደ ነበር ግለታሪካቸው ይመሰክራል፤ ከነዚህ መኻከል ዮሐንስ ኬፕለር፤ አይዛክ ኒውተን፤ ሚካኤል ፋራዳይ፤ ኤዲሴን፤ ማንዴላ፤ ጆን ሉክና ጋሊሊዩ፤ ይገኛሉ፡፡ ከፈላስፎች ውስጥም ራንሲስ ቤከን፤ ጆን ስቲዋርት፤ ሚል፤ ኢማኑኤል ካንት፤ ሄግል ይጠቀሳሉ፡፡ ከገጣምያን የሥነጽሑፍ ሰዎች ውስጥም ሼክስፒር፣ ሚልቶን፣ ቶምፕሰን፣ ጎቴ፣ ጂን፣ ጃዄስ ሮውሴእ፣ ቶሎስቶይ፣ ቼኮፍ፣ ጊብራን፣ ሚካኤል ናእማ ኤልያስ፣ አቡ ማዲ ሲጠቀሱ ከሙዚቃ ቀማሪዎች እነባች፣ ሀንዴልና ቤትሆቭን ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከሥነጥበብ ሰዎች ሚካኤል አንጀሎ፣ ራፋኤልና ሊዮናርዶ ዳቪንቺ ሲጠቀሱ ከነገሥታትና ከገዠዎች እነ ንግሥት ቪክቶሪያ፣ አብርሃም ሊነከን፣ ጆርጅ ዋሽንግተን፣ ጆን ኤፍ ኬዲ፣ ጂሚ ካርተር፣ ሮናልድ ሬገን፣ ጋንዲ፣ ግላድስቶንና ናፖሊዮን ይገኛሉ፡፡ ለዓለም ታላላቅ ሥራን ሠርተው ያለፉ እነዚህ ሁሉ ዘርፈ ብዙ ምሁራን የሕይወት ታሪካቸው እንደሚያሳየን መጽሐፍ ቅዱስ አንባብያን የነበሩና መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል መኾኑን መስክረው ያለፉ ናቸው፡፡ (መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ከላይ በገለጽኩት መሠረት በመጽሐፋቸው ላይ አስፍረውታል) የሁሉንም ስም መዘርዘር አስቸጋሪ ቢሆንም 24 የሚሆኑ በጣም የታወቁ ታላላቅ መሪዎችና ደራሲዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የሆነ ነገር ብለዋል፡፡

በሕዝባችን ዘንድ ታዲያ ይህን መጽሐፍ ለማንበብ የማይፈለገው ለምንድን ነው? የእኛ ኃላፊነት ማንም ያንበው ማን፣ እንዲነበብ የተመቻቹ ነገሮችን መፍጠር ብቻ ነው፡፡ ማንም በቅናትም ያንበው፣ በቅንነትም ይነበብ፣ ወይም በተንኮል፣ በሌላም ዓላማና ተልእኮ ቢነበብ እኛ ደስ ብሎን ማቅረብ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- “ኢየሱስ” የተባለውን የሁለት ሰዓት ፊልም ሠራው የተባለው ሰው ፊልሙን ከሠራ በኋላ ቃሉ ሕይወቱ ላይ ተጽዕኖ እንደ ፈጠረበት ገልጿል፡፡ በታሪኩ እንደ ተዘገበው ደጋግሞ ያነበበው የሉቃስ ወንጌልን ታሪክ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን አካባቢ የማያዘውትሩ፣ መንፈሳዊ መጻሕፍትንና መጽሐፍ ቅዱስን ጭምር ማንበብ የማይፈልጉ በሀገራችን ያሉ ሰዎች ሚሊዮኖች እንደሚሆኑ አልጠራጠርም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስንማ ጨርሶ ማገላበጥ መንካት የሚፈሩ እንዳሉ ከሁላችንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ቢኖራቸውም ደግሞ ከጥሩ ቦታ ወደ ጥሩ ቦታ በማዘዋወር የክብር ቦታ ማስቀመጥ እንጂ ለእነርሱ “መንካትም ሆነ ማንበብ የተከለከለ” ብለው የሚየስቡ ሕዝቦቻችንን መታደግ ያለብን ጊዜ ቢኖር ይህ የመጨረሻው ጊዜ ነው፡፡ በመቶኛ ደረጃ ብናሰላው ክርስቲያን የሆነው እንኳ ለማንበብ ተግዳሮት አለበት፡፡

ጥበብ፣ ዕድሳት፣ ለውጥ፣ ከሞራል ውድቀት መነሣት ሁሉ የሚገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የኖረችው የእንግሊዝ ንግሥት “ቪክቶሪያ” ከሞምባሳ ሊጐበኛት ለመጣ የአካባቢው ተወላጅና የጎሳ መሪና የእስልምና ተከታይ ለሆነው ሰው ንግሥቲቱ መጽሐፍ ቅዱስ ስታበረክትለት “የእንግሊዝ መንግሥት ታላቅነት ከዚህ መጽሐፍ ጀርባ ነው” በማለት ነበር፣ ታላቅ ስጦታ አድርጋ ያቀረበችው፡፡ እንግዚሊዝን የዛሬ አያድርጋትና ! ይህ ታላቅ መጽሐፍ “የኦሪት ዘፍጥረት መጀመሪያዎቹ ሦስት ምዕራፎች ገነትን እንዳጣን እንደ ነገሩን የዮሐንስ ራእይ የመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ደግሞ በበኩላቸው መንግሥተ ሰማያትን እንዳገኘን መግለጣቸውን የምናነብበት መጽሐፍ ቅዱስ ነው … እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡” ምክንያቱም ይህ ታሪክ ያለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ነውና ይሉናል አንድ ጸሐፊ፡፡ (መጋቤ ሐዲስ ሮዳ መጽሐፍ ቅዱስና የሕክምና ሳይንስ መጽሐፍ) በመጽሐፍ ቅዱስ ሽፋን በዓለም ላይ አስነዋሪ ነገር ተሠርቶ እንደ ነበረ ታሪኮች ቢዘግቡም እና ደግሞ ለሥልጣኔም ምንጭ እንደ ሆነ የብዙዎችን አእምሮ እንደ ከፈተ፤ ብሩህ እነዳደረገ ለማሳየት መጣር ይኖርብናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት መሃል የአውሮፖን ሥልጣኔ ለማመንጨት ምክንያት የሆኑት እዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን የድነት መንገድ በተረዱ ጊዜ አእምሮአቸው የተከፈተ ሰዎች ናቸውና ሳንፈራ ሳንሳቀቅ ሕዝባችን ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለውን አመለካከት እንዲለውጥ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብቻ ሳይሆን ልክ እንደ ጌዴዎናውያን በየቦታው ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው፡፡ ቃሉ አንድ ቀን፣ አንድ ቀን ሥራ ላይ መዋሉ አይቀርም፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነውን ሮሜን አንብቦ የተለወጠው ሉተር በአውሮጳ ልዩ እንቅስቃሴ እንደ ፈጠረና ያም የአእምሮ ዕድገት አምጥቶ ለዛሬው ሥልጣኔ እንዳበቃቸው አንድ የታወቁ ኢትዮጵያዊ ምሁር ገልጸውታል፡፡ (ማርቲን ሉተር በአውሮጳውያን አእምሮ ላይ ያመጣው የአስተሳሰብ ለውጥ በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን በይበልጥም በዓለማዊ ጉዳይ ላይ የለውጥ ተጽዕኖ አምጥቷል ብለዋል፡፡ ደቂቀ እስጢፋኖስ በሕግ አምላክ ገጽ14.

Anim pariatur cliche reprehenderit, enim eiusmod high life accusamus terry richardson ad squid. 3 wolf moon officia aute, non cupidatat skateboard dolor brunch. Food truck quinoa nesciunt laborum eiusmod. Brunch 3 wolf moon tempor, sunt aliqua put a bird on it squid single-origin coffee nulla assumenda shoreditch et. Nihil anim keffiyeh helvetica, craft beer labore wes anderson cred nesciunt sapiente ea proident. Ad vegan excepteur butcher vice lomo. Leggings occaecat craft beer farm-to-table, raw denim aesthetic synth nesciunt you probably haven't heard of them accusamus labore sustainable VHS.

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበርን ተጠግተን ስናየው ለምን መጽሐፍ ቅዱስ በሀገራችን በገፍ አይገባም? ለሚለው በቂ መረጃ ይገኛል፡፡ በ1997 ዓ.ም በጥር ወር ነበር የተጠጋሁት፤ የመጠጋቴ ምክንያትም የሕዝባችን የመጽሐፍ ቅዱስ ፍላጎትና አቅርቦት አልመጣጠን ሲለኝ ነበር፡፡

“ትናንት መጽሐፍ ቅዱስ አይፈልግም የተባው ሕዝብ መጽሐፍ ቅዱሰ ሲጠይቅና የለም፣ ወይም ደግሞ ያለችንም ይህችው ናት በማለት ስንመልስለትና በወቅቱ ገንዘብ ይዘን የፈለግነውን ስናጣ ወደ ጠቅላይ ጸሐፊው ቢሮ ጎራ ማለት ነበረብኝና በወቅቱ ትሕትና በሞላበት መንገድ የተቀበሉኝና ያነጋገሩኝ አቶ ይልማ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኀበርንና ሥራውን በሚመለከት ለ45 ደቂቃ ገለጻ ከሰጡኝ በኋላ በዚህ ማኀበር ጎን የቆሙትን አብያተ ክርስቲያናትን፣ ክርስቲያኖችንና ድርጅቶችን እያወደሱ ሲነግሩኝ ተደንቄ በኋላ በኋላ ግን በመልካም ጎኑ እንዳይ ያደረጉኝን የአብያተ ክርስቲያናት ተሳትፎ እኔ ደግሞ ከወንጌላውያን ጎን ራሴን አቁሜ እፍረቴን እንድከናነብ ነው ያደረገኝ፡፡ በወቅቱ 14 ሚሉዮን ያለው የወንጌላውያን ተሳትፎ በቁጥር ሲተመን ገና ከእንቅልፍ እንዳልነቃን ሲያሳይ በተጨማሪ ደግሞ የባለመብት ጥያቄው ወደ ቢሮ ሲጎርፍላቸው አስደንጋጭ ነበር፡፡ ለምን የለም ትሉናላችሁ? ለምንስ የምንፈልገውን ያህል አትሰጡንም? የመሳሰሉት የሚቀርበው ከመቶ እጅ 4% ብቻ ይሰጣል ከሚባለው ክርስቲያን መሆኑ አሳዛኝ ነበር፡፡ የቀረው 96% ገንዘብ ተገኝቶ መጽሐፍ ቅዱስ ታትሞ የሚገባው በውጭ ሀገር ርዳታ በመሆኑ ተገርሜአለሁ፡፡ ከአንድ ሺ አምስት መቶ ዓመት በላይ ክርስትና የሚነገርላት ሀገራችን እስከዛሬ የመጽሐፍ ቅዱስ እርዳታ ገንዘብ ከውጭ ማግኘቷ እንደውም ዛሬም ድረስ ለውጡ እንደ ብዛቱ አለመሆኑን እንድረዳ አድርገውኛል፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመጣ ድረስ የማያቋርጥና የሚነበብ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ እናውቃለን የተረዳን ነን ለማለት የሚዳዳን እኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች እርሱን በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ አለመቻላችን ተሳትፏችንም አናሳ መሆኑ ያሳፍራል፡፡ ዛሬም ቢሆን ስላልዘገየን ልንነቃ ይገባናል እላለሁ፡፡ በዕለቱ ባሰፈርኩት የአቶ ይልማ ንግግር ማስታወሻ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕጥረት ባለበት በደቡብ ክልል በአንድ ማረሚያ ቤት ውስጥ የነበረቻቸው አንዲት መጽሐፍ ቅዱስ መሆኗን ገልጸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች በሌሊቱ ቅደሴ ያነበቡበትን ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ የካቶሊክ ምእመናን ጧት ገደማ ተጠቅመውበት የወንጌላውያኑ ግን በ4 ሰዓት ይጠቀሙበታልና በሦስቱም አማኞች ዘንድ ስትሽከረከር መዋሏን አስረድተዋል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕጥረት ዛሬ ቢታይም የእኛን ድርሻ ለመወጣት “ብልሃት መፍጠር ወይም ራእይ ማግኘት ከቻልን መፍትሔን ማምጣት የሚቻል ይመስለኛል፡፡

ወንጌላትንና መልዕክታትን በትንንሽ እያሳተሙ ማሠራጨት በሺዎች ብቻ ሳይሆን በሚሊዮኖች ማዳረስ ያስፈልጋል፡፡ ለሙከራ ሁለት ጊዜ ዕድሉን ተጠቅመናል፡፡ የዮሐንስ ወንጌልን ማሳተም ሲሆን አሁን ደግሞ የሉቃስ ወንጌል የኮምፒውተር ሥራው እየተጠናቀቀ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ከወንጌላት አንዱን ከመልዕክታት አንዱን ወስዶ ቢያሳትም ጥማትን ለማርካት ሳይቻል አይቀርም፡፡ ይህንንም በሀገራችን ያለውን የነጻነት ዕድል ተጠቅመን እግዚአብሔርን እንድናከብረው ያሻል፡፡

በሀገራችን የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ከተመሠረተ 87 ዓመት እያለፈው ነው፡፡ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር በዚህች ሀገር ላይ “እንዲመጣ” ወይም “እንዲጀመር” አስተዋጽኦ ያደረጉትን አባቶች ዛሬም ቢሆን አንዘነጋቸውም፤ ምን ጊዜም ከባዱ ነገር “አንድን መልካም ነገር መጀመር” ነው፡፡ ከተጀመረ በኋላ በዚያ በተጀመረው ነገር ላይ መቀጠል ወይም ደግሞ ግንባታ ማድረግ ዋጋ አያስከፍልም ባልልም የጅማሬውን ያህል ግን አይሆንም ለማለት ነው፡፡ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥና ትግል ውስጥ ተጉዞ እዚህ መድረሱን ከታሪክ መዛግብት ማየት ይቻላል፡፡ ዛሬ በሁለት እግሩ ቆሟል፡፡ ይህ አንጋፋ ማኀበር በዚህች ሀገር ላይ እንዲኖር የረዳንን እግዚአብሔርን ስናመሰግን ለዚህ የተጋደሉትን የቀድሞ አባቶች እንባርካለን፡፡ ተረካቢ ትውልድ ሆነው ደግሞ በዛሬ ላይ ቆመው የሚይካሂዱትን እያመሰገንን ለብርታታቸውም መጸለይና ከጎናቸው ቆመን ተግዳሮቶችን አብረናቸው ልንወጣ ይገባል እንላለን፡፡

ይህ ማህበር ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ከካቶሊካዊትና ከወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን የተዋቀረና 24 የቦርድ አባላት ያሉበት ሲሆን በማንም ቤ/ክ ዶክትሪን ሳይገባ ሰዎች ሊያነቡ በሚችሉበት ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስን ማስተርጐም፣ ማሳተምና ማሠራጨት የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ናቸው፡፡ ክርስትናን ለማጠናከርና ዐቅም እንዲኖረው፣ ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስተላለፍም የማኀበሩ ህልውና ያስፈልገናል፡፡ ክርስትናን ያስረከቡን አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰዋል፣ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ እኛ ይህንን ብናደርግ ቢያንስ ልጆቻችን የሚረከቡት ነገር ይኖራቸዋል፡፡ ክርስቶስ እስከሚመጣ ድረስ ይህ እንዲቀጥል መደረግ ይኖርበታል፣ ለዚህም አንዱና ዋንኛው፣ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያዘጋጅልን የመጽሐፍ ቅዱስ ማኀበራችን ነው፡፡

እንግዲህ ከላይ እንደገለጽኩት አብያተ ክርስቲያናት ካላቸው የኢንፎርሜሽን ዕጥረትም ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ቤተሰብና የቅርብ ረዳት እንዲሁም ደጋፊ እንደሚጠበቀው ገና አልሆኑም ብል የምሳሳት አይመስለኝም፡፡ ማኀበሩ ገና “የእነርሱ አልሆነም” ማኀበሩ ምናልባትም የእነርሱ እንዳልሆነ የሌሎች እንደሆነ የሚያስቡም ይኖሩ ይሆናል፡፡ ማኀበሩ ምናልባት መኖሩን እንኳን የማያውቁ አሉ ብዬ ባልናገርም፣ የክርስቲያን ግዴታቸውን ግን ተወጥተዋል ወይ የሚለውን ግን በድፍረት እንድጠይቅ ይገፋፋኛል፡፡ ቢያንስ ሀገር ውስጥ ካለሁ በየዓመቱ በሚያደርገው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ሪፖርቱን ሳዳምጥ የቆጨኝን፣ በቅናት እያንገበገበኝ ያለውን መልካም ቅናት ላሳያችሁ እሻለሁ፡፡ የተገኘሁባቸው አራት ስብሰባዎች ናቸው፡፡ በ2008 ገቢ ከአብያተ ክርስቲያናት 7,260ብር፣ ከአባላት መዋጮ 104,270 ብር፤ በ2009 ከአብያተ ክርስቲያናት 6,365 ብር ከአባላትም መዋጮ157,840 ብር በ2011 ከአብያተ ክርስቲያናት 7,221 ከአባላት መዋጮ 309,923 ብር ገቢ እንደተደረገ ያመለክታል፡፡ ከዚህ ግንዛቤ ስንወስድ በአዲስ አበባ ካሉት ከ400 በላይ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት እንኳን እያንዳንዳቸው 1000 ብር በዓመት አንድ ጊዜ እንኳን ቢሰጡ 400,000 ብር ይሆን ነበር፡፡ ታዲያ ይህ የሚያሳየው የሩቅ ተመልካች መሆናችንን ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ከየትም ይምጣ ከየትም ላግኝ እንጂ የማለት ሐሳብ ወይም ጨርሶ ያለማስታወስ ካልሆነ በስተቀር፣ ክርስቲያናዊ ግዴታችን ማኀበሩን ያለበት ቦታ ፈልገን ማግኘት ይመስለኛል፡ በሀገራችን ውስጥ 20 ሚሊዮን የወንጌላውያን አማኞች ካሉ በየዓመቱ አንድ ብር እንኳን ቢከፍሉ 20 ሚሊዮን ብር ገቢ ይሆናል፡፡

እነዚህ ሲታዩ ታድያ “እኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ለመሆን ብቃት ይኖረን ይሆንን? ወይም እኛ ሊኖረን ይችላል ለሌሎች ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲደርስ ያለን ጥማትና ጉጉት ምን ያህል ነው? መጽሐፍ ቀዱስ ብቻውን ቢነበብ ያለ ሰው ማብራሪያ ያለሌላ መግለጫ የሰዎችን ሕይወት እንደሚለውጥ እናውቃለን ወይ? ሌላው እዚህ ካለነው ስንቶች መጽሐፍ ቀዱስ ከውጭ እየታተመ እንደሚመጣ ስለማወቃችን እርግጠኛ አይደለሁም መጽሐፍ ቅዱስ እስከመቼ ነው ከውጭ ሀገር እየታተመ ተጓጉዞ የሚገባው?፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ለትውልዳችን እንዲደርስ በመጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያን መሸፈን አለብን የምንል ሁሉ መረባረብ ያለብን ይመስለኛል፡፡ ሳንቀደም መቅደም ያለብንም ይመስለኛል፡፡ 90ሚሊዮን ሕዝብ እንደደረሰ የሚገመትበት ሀገር ላይ በዓመት እስከ 300ሺ መጽሐፍ ቅዱስ እየገባ እንዴት ነው ክርስትናን የምናጠናክረው እንዴትስ ነው ያለብንን ተግዳሮቶች የምንቋቋመው ? ካሉን 80 ቋንቋዎች ውስጥ በ50 ቋንቋዎች ምንም ብሉይ ኪዳንም ይሁን አዲስ ኪዳን ሳይኖረን እንዴት ነው ክርስትናን የምናስጠብቀው ? ታዲያ የዛሬዋ ቤተ ክርስቲያን ለመጽሐፍ ቅዱሳችን መስፋፋት በምድራችን መትረፍረፍ ልትጋደል ይገባታል፤ ለዚህም ከመጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ጎን በመቆም የማኀበሩ ጓደኛ በመሆን ሥራችንን እንድንቀጥል ከመቼውም ጊዜ በላይ ልናስብበት የሚገባ ጊዜ አሁን ይመስላል፡፡

የኢትዮጵያን መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ከተቀላቀልንበት ከዛሬ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድርሻችንን ለመወጣት ሞክረናል፤ አንደኛውና ዋንኛው ቤተሰባችንም ይሁን የምሥራች አገልግሎት ደጋፊዎችን የማኀበሩ አባል ማድረግ ነው፡፡ ከማኀበሩ ጎን መቆም የፈለግነው ማኀበሩን የራሳችን በማድረግ ነው፡፡ ያለ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር እንቅስቃሴ ክርስትናን እንዲቀጥል ማድረግ ከባድ ነው ብለን እናስባለን፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ይህንን ማኀበር ሰጥቶናልና በየዘመናቱ እግዚአብሔር የሚሰጣቸው ለሕዝቡ የሚጠቅሙ ነገሮች አሉና ነው፡፡

አስገራሚ ሁኔታ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር በራሴ ዕቅድ ይዤ እጓዛለሁ ብሎ ካሰበው የማስተርጐም፣ የማሳተምና የማሠራጨት አጀንዳ ውጭ በድንገት በጣም አስገራሚ የሆነ የእግዚአብሔር አጀንዳ ውስጥ ገብቷል፤ ይኸውም “አብያተ ክርስቲያናትን ማነሣሣት ነው” ወይም የሥላሴ አማኞችን ማነሣሣት ነው፡፡ በምንድነው የሚያነሳሳው? ትሉኝ ይሆናል፣ መጽሐፍ ቅዱስን አሰተርጉሞ ማዳረስ ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱሱን ወደ ተግባር መለወጥ ነው፡፡ ለዚህም ደግሞ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኀበራችን ያቀፉቸውን በሀገራችን ያሉትን የሥላሴ አማኞችን በማስተባበር ለሀገርና ለሕዝብ በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ቃሉን በተጽዕኖ ተግባር ለማዋል በሚችሉ አጀንዳዎች ላይ እየተወያዩ የክርስቶስንና የደቀመዛሙርቱን ዓላማ በተግባር እንዴት ማዋል ይቻላል? የሚል ማነሣሣት እንዲደረግ ማለት ነው፡፡

ይህ ብቻ አይደለም ለብዙ ዓመታት ባለመግባባት መንፈስ ይተያዩ የነበሩትን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያንና የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መሪዎችን ከአዲስ አበባ ጀምሮ በየክልሉ በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ በማስቀመጥ በልዩነቱ ሳይሆን አንድ በሚያደርገው ነገር እንዲወያዩ ማድረግና ዐልፈው ተርፈው ድንበር ዐልፈህ መጣኸብኝ የሚለው ሓሳብና ያለመግባባት የሚፈጥረውን ችግር በውይይት መፍታት ለማኀበሩ የተሰጠው ዋንኛ የእግዚአብሔር ሥራ ሆኖአል፡፡ ጥር 30/2001 ዓ.ም በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያቀረበችው ወረቀት የሰውን ልብ የሚያነሣሣና አብረን መሥራት አለብንን የሚያሳይ ነው፡፡ መቼም ይህንን ማስታወስ ተገቢ የመሰለኝ በወቅቱ ያልነበሩም እንዳሉ ስለማውቅና ያ ሁኔታ እንዴት ልባችንን ወደታሰበው ነገር እየወሰደው እንደሆነ መረጃዎች ስላሉ ነው፡፡ በወቅቱ ጽሑፉን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፖትርያርክ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ንቡረዕድ ኤልያስ ነበሩ፤ በተለይም በዚህች ሀገር ላይ ባለው በአሁኑ ሁኔታ ያለዚህ ምንም ማድረግ እንደማይችልም ለማስገንዘቢያ ይረዳናልና እጠቅሰዋለሁ፤ “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኀብረትን ጠቃሚነት በስፋት እንዳስተማረ ሁሉ የመለያየት ጐጂነትንም አስተምሮአል፡፡

የመለያየት ጎጂነትን ሲያስተምር “እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፤ ከተማም ሁላ፣ ቤትም እርስ በርሷ የምትለያይ ከሆነች አትጸናም ብሎአል፡፡ በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ኀብረት ከሌለ ያለው ዕድል መለያየት መሆኑን፣ መለያየት ከተከሰተ ደግሞ መዳከም የማይቀር መሆኑን፣ መለያየቱ በተራዘመ ቁጥር ደግሞ ጭራሹኑ መፍረስና መጥፋት የሚመጣ መሆኑን ዛሬም ጭምር በገሀዱ ዓለም ዕለት ተዕለት እየተፈጸመ የሚገኝ ነው፡፡ በተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ የሚሠሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው መለያየት ሲጀምሩ ድርጅቱ ከአምራችነት ወደ ኪሣራ ብሎም ወደ መዘጋት ማምራቱ ሁል ጊዜ የምናየው እውነት ነው፡፡ ይህ ችግር በቀንም ሆነ በሌሊት በሮቿ አይዘጉም የተባለላት ቤተክርስቲያንንም በምዕራቡ ዓለም እየተፈታተናት እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡ በአንድ ቤት የሚኖሩ ቤተሰቦች እርስ በርሳቸው ከተለያዩ መዳከም ብሎም መበታተን የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡

የሚገርመው ነገር ግን መለያየት ከጉዳት በስተቀር የሚያመጣው ጥቅም አለመኖሩ እየታወቀ ሰዎች ዛሬም ትዕግሥትን አንግበው አንድን ችግር በመተባበርና በመቻቻል በማስወገድ ፈንታ መለያየትን እንደ አማራጭ መፍትሔ ሲወስዱ መገኘታቸው ነው፡፡ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ከኔ ጋር ያልሆነ ባላጋራዬ ነው፣ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል ብሎአል፡፡ ይህ አባባል መለያየትን መከተል የጌታ ባላጋራ መሆን እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ከዚህ አኳያ የክርስቶስ ነን የምንል ሁላችን በመተባበር ከምንኖር ይልቅ ለመለያየት አስተዋፅኦ የምናደርግ ከሆነ የክርስቶስ ባላጋራዎቹ እየሆን እንደሆነ ከዚህ ቃል መረዳቱ ተገቢ ነው፡፡” ካሉ በኋላ የቅዱስ ጳውሎስን ቃል ጠቅሰው መለያየት የሥጋ ሥራ መሆኑንም አስምረውበታል፤ የሚገርመው ነገር ንቡረዕድ የተጨበጠውን ታሪክ ፍንትው አድርገው በወቅቱ አሳይተውን ነበር፡፡ በተለይ አስደንጋጩን ክሥተት ሲያስቀምጡት “እንግዲህ ከቅዱስ መጽሐፍ ትምህርት አንጻር ክርስቲያኖች በኀብረት እንዲኖሩ እንጂ በመለያየት እንዲኖሩ የተደገፈበት ቦታ ፈጽሞ አናገኝም፡፡ በዚህ መሠረታዊ የክርስትና የሐዋርያት ትምህርት ተልእኮዋን ስትወጣ እስከ ዐምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዘለቀችው አንዲት ቤተክርስቲያን ከተጠቀሰው ዘመን በኋላ ባጋጠማት የመለያየት አደጋ ብዙ ጉዳት ደርሶባታል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ለዐምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ሁለት፤ በዐስራ አንደኛው ክፍለ ዘመን ወደ ሦስት፣ በዐስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ወደ አራት ስትከፋፈልና መለያየት ሲበዛ ፈጣን የነበረው ተልእኮዋ በነበረበት ፍጥነት እንዳይቀጥል ልዩነቱ ደንቃራ መሰናክል ሆኖአል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ መለያየት ተፈጥሮ የኔውን ተቀበል በማለት በሚያዳክም ሁኔታ መነጋገርን ያመጣል፡፡ ከዚያም በላይ ስትከፋፈል የሚከተሉት ችግሮች ደርሰውባታል” ካሉ በኋላ ለጆሮ የሚዘገንነውንና ከአዲስ ክርስያች የማይጠበቀውን የደም መፋሰስ ጦርነት ዋና ምክንያት ሲገልጹ የመለያየቱ መንስኢ ላይ ላዩ ሲታይ በነገረ መለኮት ትምህርት የመራቀቅ ይዘት ያለው ሲመስል ከመጋረጃው በኋላ ግን የሥልጣን ሽኩቻና የሥነ ምግባር ጉድለት እንደ ነበረበት ብዙዎች ያምናሉ፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው ልዩነት ምክንያት እያንዳንዱ ጎራ ትክክለኛው አባባል የኔ ነው የሌላውን ተውት እድርገው የሚል ቅስቀሳና ትምህርት እያስከተለ ግጭትም እየተፈጠረ ነገሩ ወደ ድም መፋሰስ አምርቶአል፡፡

ይህ ድርጊት እየቀጠለ በሄደ ቁጥር በአባቶችና በምእምናን ላይ ብዙ ጉዳት እንዲደርስ ሰበብ ሆኖአል፣ በመቀጠልም በክርስትና ሃይማኖት ሥር የነበሩት ሀገሮችም እንዴት እንደተጠቁ በሚያሳዝን ሁኔታ አሳይተውናል፡፡ እንዲህ በማለት የወቅቱም አስፈሪ ችግር በዓለምም ላይ ሆነ በሀገራችንም እየተገዳደረን ነውና ንቡረዕድ ይህንን አስፍረውታል፡፡” በአራት መቶ ዓመታት ውስጥ በወቅቱ ኀያላን ተብለው የሚታወቁ የመካከለኛው አውሮፓ በሰሜንና በምሥራቅ አፍሪካ አስከ ህንድ ያሉ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች አስደናቂ በሆነ ሁኔታ በአጭር ጊዜ ክርስቶስን እንዲቀበሉ ያደረገ የወንጌል ትምህርት ብዙ ጊዜ ያልነበሩ በቀላሉ የወንጌልን ትምህርት ለመቀበል ይችሉ የነበሩ የሩቅ ምሥራቅ አገሮችና የመካከለኛ፣ የደቡብና የምዕራብ አፍሪካ ሀገሮችን ለአንደ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት ያህል ማዳረስ አቅቶት ሲያዘግም ቆይቷል ካሉ በኋላ ሲደመድሙት “ቤተ ክርስቲያን በውስጧ የተፈጠረውን ልዩነት በኀብረትና በውይይት በመፍታት ፈንታ በፉክክርና በኃይል በመፍታት ወደ ሌላው ክፍለ ዓለም እገሰግሳለሁ ብላ ላይ ታች ስትል ሳይታሰብ በድንገት የተነሡ ሌሎች ተቀናቃኝ ኃይሎች የራስዋ ይዞታ የነበሩትን ሀገሮች በቀላሉ ሊነጥቁአት ችለዋል፡፡

በዚህም ምክንያት በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ የነበሩትን የሃይማኖት ይዞታዎች በቀላሉና በአጭር ጊዘ ዐጥታለች፡፡ ይህ ሁኔታ ለቤተክርስቲያን ትልቅ ኪሳራ ተብሎ ሊቀመጥ የሚችል ነው፤ ምክንያቱም አለመስፋፋትና ባሉበት መቆም ሌላ ነገር ሆኖ በእጅ የነበረውን ነገር ማጣት ደግሞ የባሰ ክስረት ነውና፡፡ እንግዲህ አንደዚህ ያለው መጥፎ አጋጣሚ በቤተ ክርስቲያን እንደ መጣ ምክንያት ሆኖ የተገኘው መለያየት የሚባለው ክፉ ጠላት እንደሆነ ለአፍታ እንኳን ልንዘነጋው የሚገባ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቦታ ባያገኝ ኖሮ ዛሬ መላዋ ዓለም የክርስቶስ የወንጌል መድረክ ትሆን ነበር፡፡” በማለት ሰፋ ያለውን ወደ14 ገጽ የያዘውን ጽሑፋቸውን በመደምድም ክርስትናን በተጽዕኖ ወደ ሚቀጥለው ትውልድ ለማሻገር የሚቻልባቸውን ነገሮች በመጠቆም የመሪዎችን ልብ አነሣሥተዋል፡፡

የተከበራችሁ መሪዎች አባቶቻችን ያለፉበትን ትልቁን ተጋድሎ በቃሉ ዙሪያ ሆነን ለመጨረስና ለሚቀጥለው ትውልድ የተረከብነውን የክርስቲያን ሕዝብ አሻግረን ለትውልዱ ለማስረከብ ዛሬ የሀገራችን የእምነት ነጻነት የሰጠንን፣ እግዚአብሔር ያመቻቸልንን ዕድል በመጠቀም፣ ከዚህ ማኀበራችን ጎን ከመቼውም ጊዜ በላይ በመሰጠት ቆመን እንድንጓዝ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ማኀበር አለማበረታታትና ከጎኑ አለመቆም ክርስቲያናዊ ግዴታን ካለመወጣት በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሳችንን ማቀጨጭ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ማኀበሩ ሁላችንንም በዙሪያው በማሰባሰብ እንድንበረታታ እያደረገ ያለውን ሁኔታ ምንጊዜም የበለጠ እንዲያደርገው ባንዲራችንን ከፍ አድርገን እንድናውለበልብ ያስፈልጋል፡፡ እስከ ዛሬም ጽሕፈት ቤቱን የማናውቀው ካለን ማወቅ አለብን፡፡ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ጽ/ቤት የሚለው ጽሑፍ በልዩ መብራቶች በከፍታ አሸብርቆ መታየት አለበት፡፡ ለምን ብትሉኝ ይገባችኋል ሰዎች ሁሉ፣ አላፊው አግዳሚው ማንበብ አለበት፡፡ ይህ እኮ በሠለጠነው ዐለም ያሉት ትላልቅ መሪዎች እንዳሉት “ያለ እግዚአብሔርና ያለ እግዚአብሔር ቃል ከሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ዓለምን በትክክል ለማስተዳደር የማይቻል ነው” በማለት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ጆርጅ ዋሽንግተን ተናግረዋል፡፡ እንግዲህ በሁሉም ክልል ሴሚናሩ በተደረገበት ቦታ ኮሚቴዎች እየተፈጠሩ በሥራ ላይ ናቸው ! እንደዚህ ካለው ሴሚናር ውጭ በሚዲያዎች ላይ መሥራትን እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ሰዎች እጅ እንዲገባ የማድረጉን ሥራ ተያይዞታል፡፡

ገና በመንፈሳዊ አሠራር ዘልቃ በመግባት በኀብረተሰባችን ውስጥ የቃሉን ተጽዕኖ ለመፍጠር ብዙ የሚቀራትን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ማለት የሥላሴ አማኞችን የማስተባበር ሥራውን ማኀበሩ እየሠራ በመሆኑ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ መቼም ይህን ተአምራዊ አሠራር እግዚአብሔር አደረገውም ብንል የተከፈተ ልብ ሲያገኝ ነውና ለዚህ በመጀመሪያ የጠቅላይ ጸሐፊው (GENERAL SECRETARY) ቀና ልብና ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋት ያላቸው ቅንአት በመሆኑ ደስታዬ ወሰን የለውም፡፡ በተጨማሪም በማንኛውም ሥራቸው ከጎናቸው በመቆም የሚያበረታቷቸውን የማኀበሩን አገልጋዮችና ቦርዱን ሳላመሰግን አላልፍም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የሃይማኖት ብቻ መጽሐፍ አድርጎ እንዲወሐድ ፈቃድ መስጠት ያጠያይቃል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም ቦታ መግባት አለበት፡፡ መንግሥታዊ በሆኑና ባልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም በት/ቤቶች መፃሕፍት ቤት (LIBRARY) ውስጥም መግባትና መደርደር አለበት፡፡ በቅርብ የአንድ ክልል መንግሥታዊ ድርጅት ለመጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ በመጻፍ ለመጻሕፍት ቤታቸው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር፤ ይህን ዕድል እንድንጠቀም ስንጠየቅ፣ ወዲያውኑ ወደ 1200 ብር አውጥተን ከየቋንቋው የሆኑ መጽሐፍ ቅዱሶችና የመጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር ከሚያሰራጫቸው መጽሐፎች ጥቂቶቹን አበርክተናል፡፡

በሀገራችን የመንፈሳዊ ታሪክ ውስጥ፣ በት/ቤት ላይብረሪ ውስጥ በሚገኝ መጽሐፍ ቅዱስ ተመስጦ ሕይወቱ የተነካና ካለበት የሉኩሚያ በሽታ ወዲያው የተፈወሰ ሰው ታሪክ አውቃለሁ፡፡ እኛ እግዚአብሔር የሰጠንን ማንኛውም ዕድል ተጠቅመን ቃሉን ማሠራጨት ሲሆን የቀረው ድርሻ የጌታ መንፈስ ቅዱስ ይሆናል፡፡ ለዚህም እኛ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አብዝተን በመናገራችን ብዙ ተጽዕኖ ማምጣት እንዲቻል መጽሐፍ ቅዱስን በየቦታው በሚገባበት ቦታ ሁሉ ማስገባት አለብን የሚል እምነት አለኝ፡፡ የተገኙትን የሚድያ ዕድሎች ሁሉ መጠቀምም አለብን፣ ለምሳሌ እንደ ኤልሻዳይና ኢቢኤስን ለመጠቀም መጣር አለብን፡፡ መጽሔቶችን ሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናንብብ ጋር ማገናኘት መቻል አለብን፣ የቀድሞ አንዳንድ መጽሔቶች ይህንን ያደርጉ እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የሚወጡት መጽሔቶች ግን ብዙም አይታይባቸውም፣ ሰዎችን ከቃሉ ጋር ካቆራኘናቸው ቃሉ ራሱ ነጻ ያወጣቸዋል፤ መፍትሔም ይሰጣቸዋል፡፡ ቃሉ እንዳይነበብ ሰዎች በሚገባቸው ቋንቋ እንዳይዳረስ ጠላት ዲያብሎስ ያደረገውን ታጋድሎ ከላይ ጠቅሼዋለሁ፡፡ በእኛም ሀገር ተመሳሳይ ድርጊቶች ተፈጽመዋል፣ ይህንን መረዳት ያገኙትን ሰዎች በተለይ በ15ኛው ክፍለ ዘመን በቄሳሮች መንፈስ የተያዙ አንዳንድ ነገሥታት ለማጥፋት ሞክረዋል፡፡ የሰዎቻችንን ሕይወት የሚይዘው፣ በጽናት ክርስትናን እንዲያሻግሩ የሚያደርገው ቃሉ በአፋችንም በልባችንም ሲቀርብልን ነው፡፡ መስበክ ብቻ በቂ አይደለም፣ እንዲነበብ ማድረግ፣ ሰዎች በዓይናቸው እያዩ ወይም በእጃቸው እየዳሰሱ እንዲያነቡ ማድረግም አለብን፡፡ በቤተሰብ ደረጃ፣ በጎረቤት ደረጃ፣ በሰፈር ኀብረቶች ደረጃ ሁሉ ቃሉ በሥልጣን እንዲገለጽ መንገድ መፈለግ አለብን፡፡

ሠርግ ተጠርተን ስንሄድ የተሰባሪ ዕቃ ስጦታ ብቻ ይዘን ከምንሄድ “የማይሰበረውን ቃል መጽሐፍ ቅዱስንም” ይዘን ብንሄድ ምን ይመስላችኋል! አያነቡትም የእኛ አይደለም ይላሉ የሚባለውን ትተን የእኛን ድርሻ እንወጣ፡፡ አንድ ቀን ያነቡታል፡፡ ሕይወቱን ለክርስቶስ ጌታ የሰጠው የሳቅ ንጉሥ የተባለው ወንድም ቤቱን የገዛው ሰው ከገንዘቡ ጋር መጽሐፍ ቅዱስንም ጭምር ስለ ሰጠው ነው፡፡ የሚገርመው መጽሐፍ ቅዱሱን የሚያነብ የነበረው ሰክሮ ጠጥቶ ሲጨንቀው ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ከወይን ጠጅ በላይ ያሰክራልና ነጻ አወጣው፡፡ በውጭ ሀገር ያገኘኋቸው አንድ ሰው ሲነግሩኝ የተሰጠኝን መጽሐፍ ቅዱስ ለስንት ዓመት እየተንከባከብኩ በጥንቃቄ በክብር ሳስቀምጠው፣ ከቦታ ቦታ ስዘዋወር ይዤ ስዞር፣ በመጨረሻ ወደ እንግሊዝ ሀገር ስመጣ ይዤው መጣሁ፡፡ ከዚያ ማንበብ የጀመርኩት እዚህ ሀገር ሲሆን ለዘላለም ሕይወት የበቃሁትም እርሱን በማንበቤ ነው ብለውኛል፡፡

በጅቡቲ አንድ ስደተኛ ተርቦ ጋርቤጅ ውስጥ ምግብ ሲፈልግ በእርሱ አነጋገር ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማንያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ አገኘሁ፣ ብሎ ሲናገር ፊት ለፊቱ ተቀምጨ ነበር፡፡ በእጄ እንደዚህ ዓይነት መጽሐፍ ስነካ መጀመሪያ ጊዜ ነው። እኔ የፖለቲካ ሰው እንጂ የሃይማኖት ሰው አይደለሁም፣ ሆኖም በወቅቱ ለሥጋዬ ምግብ ስፈልግ ለካ የሚያስፈልገኝ ምግብ የነፍስ ነበር፡፡ አለ ይህ ወጣት፣ በደርግ ጊዜ በኢሕአፓ ፖለቲካ ውስጥ የነበረ ሰውና ሊረሸኑ ከተመደቡት መሃል በተዓምር የወጣ ወይም እንዲያመልጥ የተደረገ ሰው ነው፡፡ ከዚያም ይላል ገለጥ ሳደርገው “በማሕፀን ሳልሠራህ ዐውቄሃለሁ፣ ከማሕፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፣ ለአሕዛብ ነቢይ አድርጌሃለሁ፡፡” የሚለውን ከትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ አንድ ነበር ያነበበው፡፡ ታዲያ ይህ ቃል በውስጡ በፈጠረው ተጽፅኖ ሕይወቱ ተለውጦ ዛሬ በውጭ ሀገር የወንጌል አገልጋይ ነው፡፡

አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ኃላፊነታቸው ሰፊ በመሆኑ ቃሉን ለማዳረስ ሌሎች መንገዶችንም ማሳየት መልካም ነው፡፡ ለምሳሌ የተለያዩ የጥያቄ ውድድሮች በማድረግ ከፍተኛ ሽልማት እያዘጋጀን መስጠት ብንችል ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያነቡ ማደፋፈር አይሆንምን? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች ውድድር ልክ በ ETV እንደሚቀርበው ዓይነት በየቤተክርስቲያኑ በተለይም ለወጣቶች በማቅረብ ለመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፍላጎት በሩን ማስከፈት አለብን፡፡ ምናልባትም ይህ ውድድር በውጭ ያሉትን መጽሐፍ ቅዱስ የማያነቡትን ሁሉ እንዲያነቡ የሚያደፋፍር አይሆንምን ? መጽሐፍ ቅዱስና ኢትዮጵያ ያላት መልክ በጥቂቱ ይህንን ሲመስል፣ ጉባኤው ደግሞ ማዳበሪያ ሊጨምርበት፣ ወይም የድርጅቱ መሪዎች ካልመጡ ይህንን ዐውደ ጥናት ለዋና መሪዎቹ በማቅረብ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉት ማንኛውም አገልጋዮችም እንዲያውቁትና በዚህ በማኀበሩ ሥራ ውስጥ ተሳትፎአቸውን እንዲያበረክቱ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ እንዴት ነው እኛ የምንሳተፈው ሌሎችም እንዲሳተፉ የምናደርገው? የሚለየውን በውይይቱ ላይ ማንሣት ይቻላል፡፡ እንግዲህ ጸሎቴ የነበረው እንደ ንጉሥ ዳዊት “እስካረጅ እስክሸመግልም ድረስ ለሚመጣው ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ አቤቱ አትተወኝ” ነበርና፣ከዚህ በላይስ ምን ጸሎት አለ?